Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 40:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ “የጌታን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጎዳና በበረሀ አስተካክሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንዲህ ይላል፤ “በምድረ በዳ የጌታን መንገድ፣ አዘጋጁ፤ ለአምላካችን አውራ ጐዳና፣ በበረሓ አስተካክሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እንዲህ የሚል ድምፅ ይሰማል፦ “በምድረ በዳ የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ! በበረሓም ለአምላካችን ጥርጊያ ጐዳና አብጁ!

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የዐ​ዋጅ ነጋሪ ቃል በም​ድረ በዳ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጥረጉ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ጎዳና በበ​ረሃ አስ​ተ​ካ​ክሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጎዳና በበረሀ አስተካክሉ።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 40:3
16 Cross References  

እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትደሰቱበትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


እርሱም “ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለ ‘የጌታን መንገድ አቅኑ’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ ነኝ” አለ።


እርሱም፦ “ጥረጉ፥ መንገድን አዘጋጁ፥ ከሕዝቤም መንገድ ዕንቅፋትን አስወግዱ” ይላል።


እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ ይህን እናንተም አታውቁም? በምድረ በዳም መንገድን በበረሃም ወንዞችን እዘረጋለሁ።


በዚያም አውራ ጎዳና ይኖራል፥ እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል፤ ንጹሐን ያልሆኑ አያልፉበትም፥ የእርሱ የሆኑ ሕዝቦች ግን ያልፉበታል፤ ተጓዦች ሆኑ፥ ሰነፎች እንኳ አይስቱበትም።


ተራሮቼንም ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፥


ጻድቃንም ደስ ይበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ፥ በደስታም እልል ይበሉ።


ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጉጡም ሜዳ ይሆናል፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements