ኢሳይያስ 40:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 አላወቅህም? አልሰማህም? ጌታ የዘለዓለም አምላክ ነው፤ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፤ አይታክትም፤ ማስተዋሉም አይመረመርም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም28 አታውቅምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፣ የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው። አይደክምም፤ አይታክትም፤ ማስተዋሉም በማንም አይመረመርም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 ከቶ አታውቅምን? ከቶስ አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘለዓለም አምላክ ነው፤ ዓለምን ሁሉ የፈጠረ እርሱ ነው፤ እርሱ ከቶ አይደክምም ወይም አይታክትም፤ ሐሳቡን መርምሮ ሊደርስበት የሚቻለው የለም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 አሁንም አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘለዓለም አምላክ፥ የምድርንም ዳርቻ የፈጠረ አምላክ ነው፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ ማስተዋሉም አይመረመርም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፥ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። See the chapter |