Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 39:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እነሆ፥ በቤትህ ያለውን ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አይቀርም፥ ይላል ጌታ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እነሆ፤ በቤተ መንግሥትህ ያለው ሁሉ፣ አባቶችህ እስከዚህች ቀን ድረስ ያከማቹትም ሁሉ ወደ ባቢሎን ተማርኮ የሚወሰድበት ቀን ይመጣል፤ አንዳች የሚተርፍ ነገር የለም፤ ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የቀድሞ አባቶች እስከዚህች ቀን ያከማቹት በቤተ መንግሥትህ ያለው ሀብት ሁሉ ተጠራርጎ ወደ ባቢሎን የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ ምንም ነገር አይቀርልህም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እነሆ፥ በቤ​ትህ ያለው ሁሉ፥ አባ​ቶ​ች​ህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከ​ማ​ቹት ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን የሚ​ፈ​ል​ስ​በት ወራት ይመ​ጣል፤ ምንም አያ​ስ​ቀ​ሩ​ል​ህም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እነሆ፥ በቤትህ ያለውን ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፥ ምንም አይቀርም፥ ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 39:6
11 Cross References  

በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት የነበረውን ሀብት ሁሉ ጠራርጎ ወደ ባቢሎን ወሰደ። ቀደም ሲል እግዚአብሔር በተናገረውም ቃል መሠረት ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አሠርቶት የነበረውን የወርቅ ዕቃ ሁሉ ሰባበረው።


የዚህችንም ከተማ ባለጠግነት ሁሉ ጥሪትዋንም ሁሉ ክብርዋንም ሁሉ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እነርሱም ይበዘብዙአቸዋል ይዘውም ወደ ባቢሎን ያመጡአቸዋል።


የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላቁንና ታናሹን፥ የጌታንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንና የሹማምንቱን መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።


ዓመቱ ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደናፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፥ የከበረውንም የጌታን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ ወንድሙንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ።


ልብስሽን ይገፍፉሻል የሚያማምሩ ጌጣጌጦችሽን ይወስዳሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements