Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 38:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጌታ ያድነኛል፤ ስለዚህ በዕድሜያችን ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት ቅኔዎችን አውታር ባለው መሣሪያ እንዘምራለን።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እግዚአብሔር ያድነኛል፤ ስለዚህ በዕድሜ ዘመናችን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ አውታር ባለው መሣሪያ እንዘምራለን።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እግዚአብሔር ያድነኛል፤ ስለዚህ እኛ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ አውታር ባለው የሙዚቃ መሣሪያ የምሥጋና መዝሙር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንዘምራለን።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጌታዬ ሆይ አንተ መድ​ኀ​ኒቴ ነህ፤ ስለ​ዚህ በሕ​ይ​ወቴ ዘመን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አው​ታር ባለው ዕቃ አን​ተን ማመ​ስ​ገ​ንን አላ​ቋ​ር​ጥም።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እግዚአብሔር ያድነኛል፥ ስለዚህ በዕድሜያችን ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ቅኔዎችን አውታር ባለው ዕቃ እንዘምራለን።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 38:20
19 Cross References  

ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና በዘመኔ ሁሉ እጠራዋለሁ።


በከበሮና በሽብሸባ አወድሱት፥ በባለ አውታር መሣሪያና በእምቢልታ አወድሱት።


በየቀኑ ሁሉ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም ለዘለዓለም ዓለምም አመሰግናለሁ።


ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎቼም ላይ ያስሄደኛል። ለመዘምራን አለቃ፥ በባለ አውታር መሣሪያዎቼ።


አምላክ ሆይ ጉዞህን አዩት፥ የአምላኬና የንጉሤ ንግደት ወደ ቤተ መቅደስ።


ለሕግ ተላላፎች መንገድህን አስተምራለሁ፥ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ።


ጌታን በመሰንቆ አመስግኑት፥ ዐሥር አውታርም ባለው በገና ዘምሩለት።


የዳዊት መዝሙር። ጻድቃን ሆይ፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ፥ ለቅኖች ምስጋና ይገባል።


እግሮችህ በደም ይረገጡ ዘንድ፥ የውሾችህ ምላስ በጠላቶች ላይ ይሆን ዘንድ።


በሕይወቴ ሳለሁ ለጌታ እቀኛለሁ፥ ለአምላኬም በምኖርበት ዘመን ሁሉ እዘምራለሁ።


በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ጌታን አመሰግናለሁ፥ በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ።


የዳዊት የምስጋና መዝሙር። አምላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥ ስምህንም ለዘለዓለም ዓለምም እባርካለሁ።


እነሆ፤ ጌታ መዳኛዬ ነው፤ እታመናለሁ፤ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ የመዳኔ ምክንያትም ሆኖአል።”


እኔ ግን ከምስጋና ቃል ጋር እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እፈፅማለሁ። ደኅንነት ከጌታ ነውና።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements