ኢሳይያስ 36:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ስለ ሰረገሎችና ስለ ፈረሰኞች በግብጽ ስትታመን፥ ከአለቃዬ ባርያዎች የሚያንሰውን የአንዱን አለቃ ፊት ለመቃወም እንዴት ይቻልሃል? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 የምትመካው በግብጽ ሠረገሎችና ፈረሶች ሆኖ ሳለ ከጌታዬ የበታች የጦር ሹማምት እንኳ አንዱን እንዴት መመለስ ትችላለህ? See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 አንተ ከአሦራውያን ባለሥልጣኖች የመጨረሻውን ዝቅተኛ መኰንን እንኳ ለመቋቋም የምትችል አይደለህም፤ ይህም ሆኖ ግብጻውያን ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ይልኩልኛል ብለህ ተስፋ ታደርጋለህ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ከታናናሾቹ ከጌታዬ አገልጋዮች የሚያንሰውን የአንዱን ጭፍራ ፊት መመለስ እንዴት ትችላለህ? ስለ ሰረገሎችና ፈረሰኞች በግብፅ የሚታመኑ ለጌታዬ ባሮች ናቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ስለ ሰረገሎችና ስለ ፈረሰኞች በግብጽ ስትታመን፥ ከጌታዬ ባሪያዎች የሚያንሰውን የአንዱን አለቃ ፊት ትቃወም ዘንድ እንዴት ይቻልሃል? See the chapter |