| ኢሳይያስ 36:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ሕዝቅያስ፥ ጌታ በእርግጥ ያድነናል ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም፥ ብሎ በጌታ እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።See the chapter አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ደግሞም ሕዝቅያስ፣ ‘እግዚአብሔር በርግጥ ያድነናል፤ ይህች ከተማ ለአሦር ንጉሥ ዐልፋ አትሰጥም’ እያለ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።See the chapter አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ሕዝቅያስ ‘በእግዚአብሔር ተማመኑ፤ እርሱ ያድነናል፤ ከተማችንም በአሦራውያን ሠራዊት እጅ እንዳትገባ ይከላከልልናል’ እያለ የሚያግባባችሁን አትስሙት።See the chapter የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ሕዝቅያስም፦ እግዚአብሔር በእርግጥ ያድናችኋል፤ ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም አይበላችሁ።See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ሕዝቅያስም፦ እግዚአብሔር በእርግጥ ያድነናል ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም ብሎ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።See the chapter |