ኢሳይያስ 36:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ከዚያም ኤልያቄም፥ ሳምናስና ዮአስ ራፋስቂስን፦ “እኛ እንሰማለንና እባክህ፥ በሚገባን በሶርያ ቋንቋ ለአገልጋዮችህ ተናገር፤ በቅጥርም ላይ ባለው ሕዝብ መግባቢያ በአይሁድ ቋንቋ አትናገረን” አሉት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ኤልያቄም፣ ሳምናስና ዮአስ የጦር አዛዡን፣ “እኛ አገልጋዮችህ ስለምንሰማ፣ እባክህን በሶርያ ቋንቋ ተናገር፤ በቅጥሩ ላይ ያሉት ሰዎች በሚሰሙት በዕብራይስጥ አትናገረን” አሉት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ከዚህ በኋላ ኤልያቄም፥ ሼብናና ዮአሕ የአሦራውያኑን ባለ ሥልጣን “እኛ ትርጒሙን ስለምናውቅ በሶርያ ቋንቋ እንድትነግረን እንለምንሃለን፤ በቅጽር ላይ ያሉት ሕዝብ ሁሉ በሚሰሙት በዕብራይስጥ ቋንቋ አትንገረን” አሉት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ኤልያቄምና ሳምናስ፥ ዮአስም ራፋስቂስን፥ “እኛ እንሰማለንና እባክህ፥ በሶርያ ቋንቋ ለባሪያዎችህ ተናገር፤ በቅጥርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በዕብራይስጥ አትናገረን” አሉት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ኤልያቄምና ሳምናስ ዮአስም ራፋስቂስን፦ እኛ እንሰማለንና እባክህ፥ በሶርያ ቋንቋ ለባርያዎችህ ተናገር፥ በቅጥርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በአይሁድ ቋንቋ አትናገረን አሉት። See the chapter |