Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 36:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አሁንም ቢሆን፥ ጌታ፦ ወደዚህ አገር ወጥተህ አጥፋው አለኝ እንጂ፥ በውኑ ያለ ጌታ ይህን አገር ለማጥፋት የዘመትኩ ይመስልሃል?”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ደግሞስ ይህን ምድር ለማጥቃትና ለማጥፋት የመጣሁት ያለ እግዚአብሔር ይመስልሃልን? በዚህች አገር ላይ ዘምቼ እንዳጠፋት የነገረኝ ራሱ እግዚአብሔር ነው።’ ”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እኔስ ብሆን ይህንን አገር ለመውረርና ለማጥፋት የቻልኩት ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ይመስልሃልን? እንዲያውም በአገሪቱ ላይ አደጋ ጥዬ እንዳጠፋት ያዘዘኝ እግዚአብሔር ራሱ ነው።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሁ​ንም በውኑ ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እና​ጠ​ፋ​ችሁ ዘንድ ወደ​ዚህ ሀገር ዘም​ተ​ና​ልን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ ሀገ​ራ​ቸው ዘም​ታ​ችሁ አጥ​ፉ​አ​ቸው” አለን።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አሁንም በውኑ ያለ እግዚአብሔር ይህን አገር አጠፋ ዘንድ ወጥቻለሁን? እግዚአብሔር፦ ወደዚህ አገር ወጥተህ አጥፋው አለኝ።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 36:10
8 Cross References  

እኔ በአንተ አገር ላይ አደጋ የጣልኩባትና የደመሰስኳት ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ይመስልሃልን? እግዚአብሔር ራሱ በዚህች አገር ላይ አደጋ እንድጥልባትና እንድደመስሳት አዞኛል።”


ከዚህ በኋላ ከቤትኤል የመጣው ሽማግሌ ነቢይ “እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከጌታ የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል” አለው፤ ነገር ግን ዋሽቶ ነበር።


ኒካዑም እንዲህ ብሎ መልእክተኞችን ላከበት፦ “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ! እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? ውግያ የማደርገው በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአንተ ላይ ዛሬ አልመጣሁም፤ ጌታም እንድቸኩል አዝዞኛል፤ ከእኔ ጋር ያለው ጌታ እንዳያጠፋህ ይህን በእርሱ ላይ ከማድረግ ተመለስ።”


ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ቢነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ ጌታ ካላደረገው በቀር በከተማ ላይ ክፉ ነገር ይሆናልን?


እኔ ግን መቀመጫህንና መውጫህን መግቢያህንም በእኔም ላይ የተቈጣኸውን ቁጣ አውቄአለሁ።


ስለዚህ አክዓብ አራት መቶ የሚሆኑትን ነቢያቱን ጠርቶ “ወደ ራሞት ሄጄ አደጋ ልጣልባት ወይስ ልተው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “ሄደህ አደጋ ጣልባት፤ ጌታም ድልን ያቀዳጅሃል” ሲሉ መለሱለት።


ሌሎቹም ነቢያት ይህንኑ ቃል በመደገፍ “በራሞት ላይ ዝመት፤ ታሸንፋለህ፤ ጌታም ድልን ይሰጥሃል” አሉት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements