Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 34:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሰይፌ በሰማይ ሆና ጠጥታ በምትረካበት ጊዜ፥ እነሆ፥ በኤዶምያስና በረገምሁት ሕዝብ ላይ ለፍርድ ትወርዳለች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሰይፌ በሰማያት እስኪበቃት ጠጥታለች፤ እነሆ፤ ወደ ኤዶም፣ ፈጽሞ ወዳጠፋሁት ሕዝብ ለፍርድ ወርዳለች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የእግዚአብሔር ሰይፍ በሰማያት ያቀደውን ካደረገ በኋላ ጥፋትን በወሰነበት በኤዶም ሕዝብ ላይ ለመፍረድ ይወርዳል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሰይፌ በሰ​ማይ ሆና ሰከ​ረች፤ እነሆ፥ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስና በሚ​ጠ​ፉት ሕዝብ ላይ ለፍ​ርድ ትወ​ር​ዳ​ለች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሰይፌ በሰማይ ሆና እስክትረካ ድረስ ጠጥታለች፥ እነሆ፥ በኤዶምያስና በረገምሁት ሕዝብ ላይ ለፍርድ ትወርዳለች።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 34:5
32 Cross References  

ያ ቀን የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን ነው፤ እርሱም ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን ነው፤ ሰይፍ በልቶ ይጠግባል በደማቸውም ይሰክራል፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መሥዋዕት አለውና።


ኤዶም፦ “እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን” ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ የክፋት አገር፥ ጌታ ለዘለዓለም የተቆጣው ሕዝብ ብለው ይጠሩአቸዋል።”


ይህ ከኤዶምያስ፥ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፥ አለባበሱ ያማረ፥ በጉልበቱ ጽናት የሚራመድ ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ።”


ከዚህ በኋላ በግራው ያሉትን ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ።


እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።


አንተ የጌታ ሰይፍ ሆይ! ዝም የማትለው እስከ መቼ ነው? ወደ ሰገባህ ግባ ጸጥ ብለህም ዕረፍ።


ስለዚህ መርገም ምድርን ትበላለች፥ ነዋሪዎቿም ስለ ጥፋታቸው ይቀጣሉ፤ ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይቃጠላሉ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።


አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ፦ እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ ያሉአትን።


አቤቱ፥ ተነሥ፥ ቀድመህ ወደ ታች ጣለው፥ ነፍሴን ከኃጢአተኛ በሰይፍህ አድናት።


የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውንም ወተት፥ ከሰቡት በጎችና ፍየሎች ጋር፥ የባሳንንም አውራ በጎች፥ ፍየሎችም፥ ከምርጥ ስንዴ ጋር በላህ፥ ከወይኑም ዘለላ የወይን ጠጅ ጠጣህ።”


በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፤ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኃይል እንደሚያበራ እንደ ፀሐይ ነበረ።


ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትንም የማይተዉ ዐይኖች አላቸው፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው።


ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ ከርግማን በታች ናቸው፤ “በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ይሁን፤” ተብሎ ተጽፎአልና።


ጌታን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ! ና!


ስለዚህ የመቅደሱን አለቆች አረከስኩ፥ ያዕቆብንም እርግማን፥ እስራኤልንም ስድብ አደረግሁ።


እድላችሁን ለሰይፍ አደርገዋለሁ፥ ሁላችሁም ለመታረድ ትጐነበሳላችሁ፤ በፊቴም ክፉ ነገርን አደረጋችሁ፥ ያልወደድሁትንም መረጣችሁ እንጂ በጠራኋችሁ ጊዜ አልመለሳችሁልኝም፤ በተናገርኩም ጊዜ አልሰማችሁኝም።


ኤዶምያስ እና ነገሥታቶችዋ አለቆችዋም ሁሉ በዚያ አሉ፤ ኃይል የነበራችው በሰይፍ ከተገደሉት፥ ካልተገረዙት እና ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተኝተዋል።


የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


ተራሮቹንም በተገደሉት ሰዎች እሞላለሁ፤ በኮረብቶችህ፥ በሸለቆዎችህና በውሃ መውረጃዎችህ ሁሉ ላይ በሰይፍ የተገደሉት ይወድቃሉ።


የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በመሆኑ እንደተደሰትህ፥ እንዲሁ አደርግብሃለሁ፤ የሴይር ተራራ ሆይ፥ አንተ፥ ኤዶም ሁሉና ሁለንተናዋ ባድማ ትሆናላችሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ስለ ኤዶሚያስ የተነገረ ሸክም። አንዱ ከሴይር፦ “ጉበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው? ጉበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው?” ብሎ ጠራኝ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ፤


በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ! የጌታ ቀን ቀርቧልና፤ ጌታ መሥዋዕትን አዘጋጅቷል የጠራቸውንም ቀድሶአል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements