ኢሳይያስ 34:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 በጌታ መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም፤ የጌታ አፍ አዝዞአልና፥ መንፈሱ ሰብስቦአቸዋልና ከእነዚህ አንዲት አትጠፋም፥ ጥንዱን የሚያጣ የለም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 በእግዚአብሔር መጽሐፍ እንዲህ የሚለውን ተመልከቱ፤ አንብቡም፤ ከእነዚህ አንዱ አይጐድልም፤ እያንዳንዷም አጣማጇን አታጣም፤ ይህ ትእዛዝ ከአፉ ወጥቷል፤ መንፈሱ በአንድ ላይ ይሰበስባቸዋልና። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ስለ ሕያዋን ፍጥረት ሁሉ በእግዚአብሔር መጽሐፍ የተጻፈውን ፈልጋችሁ አንብቡ፤ ከእነዚህ ፍጥረቶች አንዱ እንኳ አይጠፋም፤ የኑሮ ጓደኛ አጥቶ ብቻውን የሚኖርም አይገኝም፤ እግዚአብሔር ራሱ ይህ እንዲሆን ስላዘዘ እርሱ ራሱ በኅብረት እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 በየቍጥራቸው ያልፋሉ፤ ከእነርሱም አንዱ አይጠፋም፤ እርስ በርሳቸው አይተጣጡም፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አዝዞአቸዋልና መንፈሱም ሰብስቦአቸዋልና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 በእግዚአብሔር መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም፥ አፌ አዝዞአልና፥ መንፈሱ ሰብስቦአቸዋልና ከእነዚህ አንዲት አትጠፋም፥ ባልንጀራውንም የሚያጣ የለም። See the chapter |