Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 34:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በአዳራሾችዋም እሾህ፥ በቅጥሮችዋም ሳማና አሜከላ ይበቅሉባታል፤ የቀበሮም ማደሪያና የሰጎን ሥፍራ ትሆናለች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በቅጥር የተመሸጉ ከተሞቿን እሾኽ፣ ምሽጎቹንም ሳማና አሜከላ ይወርሷቸዋል፤ የቀበሮዎች ጕድጓድ፣ የጕጕቶችም መኖሪያ ትሆናለች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ቤተ መንግሥቶችዋና በቅጽር የተመሸጉ ከተሞችዋ ሁሉ እሾኽና ሳማ ይበቅልባቸዋል፤ የቀበሮና የሰጐን መኖሪያዎች ይሆናሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በከ​ተ​ማ​ዎ​ች​ዋም እሾህ፥ በቅ​ጥ​ሮ​ች​ዋም አሜ​ከላ ይበ​ቅ​ሉ​ባ​ታል፤ የአ​ጋ​ን​ንት ማደ​ሪ​ያና የሰ​ጎን ስፍራ ትሆ​ና​ለች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በአዳራሾችዋም እሾህ በቅጥሮችዋም ሳማና አሜከላ ይበቅሉባታል፥ የቀበሮም ማደሪያና የሰጎን ሥፍራ ትሆናለች።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 34:13
17 Cross References  

የወሬን ድምፅ ስሙ፤ እነሆም፥ የይሁዳን ከተሞች ባድማና የቀበሮ ማደሪያ ሊያደርጋቸው ከሰሜን ምድር ጽኑ ሽብር መጥቷል።


ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፥ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይቀመጥባት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”


ዔሳውን ግን ጠላሁት፤ ተራራውን አጠፋሁ፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች ሰጠኋቸው።


ልባችን ወደ ኋላው አልተመለሰም፥ ፍለጋችንም ከመንገድህ ፈቀቅ አላለም፥


በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኩሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኩሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ ይሆናሉ፥ አረም እንደ ዋጠው ስፍራና እንደ ጨው ጉድጓድ ለዘለዓለምም ይጠፋሉ፤ የሕዝቤም ትሩፍ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።


እነሆ፥ ከጥፋት ሸሽተው ቢሄዱ እንኳ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፥ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች፤ ሳማም የብራቸውን ጌጥ ይወርሰዋል፥ እሾኽም በድንኳኖቻቸው ውስጥ ይበቅላል።


ባቢሎንም የፍርስራሽ ክምር፥ የቀበሮ ማደሪያ ሰውም የማይቀመጥባት መሣቀቅያና ማፍዋጫ ትሆናለች።


አሦርም የቀበሮዎች መኖሪያና የዘለዓለም ባድማ ትሆናለች፤ በዚያም ማንም ሰው አይኖርም፥ የሰው ልጅም አይቀመጥባትም።”


ደረቂቱ ምድር ኩሬ፥ የተጠማች መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች፤ ቀበሮ የተኛበት መኖሪያ ለምለም፥ ሸምበቆው ደንገል ይበቅልበታል።


ከተማይቱን የድንጋይ ክምር፥ የተመሸገችውን ከተማ ውድማ እንድትሆን፥ የኀጥኣንንም አዳራሽ ከተማ እንዳትሆን አድርገሃል፤ ደግማም አትገነባም።


ጋሜል። ቀበሮች እንኳ ጡቶታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፥ የወገኔ ልጅ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካኝ ሆነች።


ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፥ ሰውም የማይቀመጥባቸው የሰውም ልጅ የማያልፍባቸው ምድር ሆኑ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements