Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 32:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ሆይ፥ ወይንን መቁረጥ ይጠፋልና፥ ፍሬም ማከማቸት አይመጣምና ከዓመትና ከጥቂት ቀን በኋላ ትንቀጠቀጣላችሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ዓመቱ ገና እንዳለፈ፣ ተደላድላችሁ የነበራችሁ ትንቀጠቀጣላችሁ፤ የወይን ተክል ፍሬ አይሰጥም፤ የፍራፍሬም ወቅት አይመጣም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እናንተ በኑሮአችሁ የተማመናችሁ ሴቶች ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተስፋ የሚያስቈርጥ ጭንቀት ይደርስባችኋል፤ ከወይንም ሆነ ከሌላው ተክል ሁሉ በቂ ፍሬ አታገኙም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በየ​ዓ​መቱ የኀ​ዘን በዓል መታ​ሰ​ቢያ አድ​ርጉ፤ ወይን መቍ​ረጥ አል​ፎ​አል፤ ፍሬ ማከ​ማ​ች​ትም አል​ቆ​አል፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​መ​ጣም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ሆይ፥ ወይንን መቍረጥ ይጠፋልና፥ ፍሬም ማከማቸት አይመጣምና ከዓመትና ከጥቂት ቀን በኋላ ትንቀጠቀጣላችሁ።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 32:10
14 Cross References  

ፈጽሜ አጠፋችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በወይን ላይ ፍሬ፥ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ አይሆንም፥ ቅጠልም ይረግፋል፤ የሰጠኋቸሁም ይጠፋባቸዋል።


በዚያን ቀን ሺህ ሰቅል ብር የሚያወጣ አንድ ሺህ የወይን ተክል የነበረበት ቦታ ሁሉ፤ ኩርንችትና እሾኽ ብቻ ይሆናል።


ሀብታቸው ይዘረፋል፥ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፤ ቤቶችንም ይሠራሉ፥ ነገር ግን አይኖሩባቸውም፤ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁን ግን አይጠጡም።


የበለስ ዛፍ ባታብብም፥ በወይን ተክሎች ላይ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ምርት ቢቋረጥ፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ከብቶችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥


ወይኑ ደርቆአል፥ በለሱም ጠውልጎአል፥ ሮማኑና ተምሩ እንኰዩም የምድርም ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፥ ደስታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆአል።


ወይኔን ባዶ ምድር አደረገው፥ በለሴንም ሰበረው፥ ባዶም አደረገው፥ ጣለውም፥ ቅርንጫፎቹም ነጡ።


የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፤


እንዲሁም አሁን ውሽሞችዋ እያዩ ነውርዋን እገልጣለሁ፤ ከእጄም ማንም አያድናትም።


ደስታና ሐሴትም ከፍሬያማው እርሻ ተወስዶአል፤ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና እልልታ የለም፤ በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ።


አዲስ የወይን ጠጃችሁ ከአፋችሁ ተወግዶአልና እናንተ ሰካራሞች፥ ነቅታችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የወይን ጠጅ የምትጠጡ ሁሉ፥ ዋይ በሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements