ኢሳይያስ 30:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 በሌሊት የተቀደሰ በዓል ስታከብሩ እንደምትዘምሩ ዝማሬ፥ ወደ ጌታም ተራራ ወደ እስራኤል ዐለት እንቢልታ ይዞ በእልልታ እንደሚወጣ ሰው የልብ ሐሴትን ያደርጋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 በሌሊት የተቀደሰ በዓል ስታከብሩ እንደምትዘምሩ፣ ትዘምራላችሁ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ እስራኤል ዐለት፣ ሰዎች ዋሽንት እየነፉ በደስታ እንደሚወጡ፣ የእናንተም ልብ እንዲሁ ሐሤት ያደርጋል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 እናንተ ግን ደስ ይላችኋል፤ በተቀደሰ በዓል ምሽት እንደምትዘምሩት ትዘምራላችሁ፤ የእስራኤል አምባ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዋሽንት እየነፉ እንደሚዘምሩት ሰዎች ትደሰታላችሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 በዐልን እንደሚያከብሩ፥ ሁልጊዜ ደስ ሊላችሁ፥ ወደ ተቀደሰው ቦታየም ልትሄዱ አይገባችሁምን? በእግዚአብሔር ተራራ ደስ እንደሚላቸው በእንቢልታ ወደ እስራኤል ቅዱስ ልትሄዱ ይገባችኋል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 ዝማሬ በተቀደሰች የዐውደ ዓመት ሌሊት አንደሚሆን ዝማሬ ይሆንላቸዋል፥ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ እስራኤል አምባ ይመጣ ዘንድ እንቢልታ ይዞ እንደሚሄድ ሰው የልብ ደስታ ይሆንላችኋል። See the chapter |