Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 30:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጌታም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ቢሰጥህም አስተማሪህ እንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፤ ዐይኖችህ ግን አስተማሪህን ያያሉ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ጌታ የጭንቀት እንጀራና የመከራ ውሃ ቢሰጥህም፣ አስተማሪህ ከእንግዲህ አይሰወርብህም፤ ዐይኖችህም አስተማሪህን ያያሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በብዙ መከራ ውስጥ እንድታልፉ እግዚአብሔር ይፈቅድ ይሆናል፤ ነገር ግን እርሱ ራሱ ከእናንተ ጋር በመገኘት ያስተምራችኋል፤ ዳግመኛም እርሱን በመፈለግ አትደክሙም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የጭ​ን​ቀ​ትን እን​ጀ​ራና የመ​ከ​ራን ውኃ ይሰ​ጥ​ሃል። የሚ​ያ​ሳ​ስ​ቱ​ህም እን​ግ​ዲህ ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ቡም፤ ዐይ​ኖ​ችህ ግን የሚ​ያ​ሳ​ስ​ቱ​ህን ያያሉ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ጌታም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ቢሰጥህም አስተማሪህ እንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፥ ዓይኖችህ ግን አስተማሪህን ያያሉ፥

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 30:20
17 Cross References  

የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ በሕዝብህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈጣለህ?


እኔም በደኅና እስክመለስ ድረስ በእስር ቤት አስገብተው ደረቅ እንጀራና ውሃ ብቻ እየሰጡት እንዲቆይ ያደርጉ ዘንድ በእኔ ስም ንገራቸው” ሲል አዘዘው።


እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥ ማለዳ መነሣታችሁ፥ አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው። እርሱ ለሚወዱት እንቅልፍን ይሰጣልና።


ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ አይኖርም፥ ይህም እስከ መቼ እንደሚቆይ የሚያውቅ በኛ ዘንድ የለም።


ጠላቶቼ ሁልጊዜ ይሰድቡኛል፥ የሚያሳድዱኝም በእኔ ስም ይራገማሉ።


ቅዱሳን ሆይ፥ ለጌታ ዘምሩ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።


የቦካውን ቂጣ ከእርሱ ጋር አትብላ፥ ከግብጽ አገር በችኮላ ስለ ወጣህ ከግብጽ አገር የወጣህበትን ቀን በዕድሜህ ሁሉ ታስብ ዘንድ ይህን ቂጣ፥ እርሱም የመከራን እንጀራ፥ ሰባት ቀን ከእርሱ ጋር ብላ።


አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ የሰጠ እርሱ ነው፤


እንግዲህ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ የመከሩን ጌታ ለምኑት።”


እናንተም እንዲህ በሉ፦ ‘ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ በደኅና እስክመለስ ድረስ ይህን ሰው በወህኒ ቤት አኑሩት፥ የመከራም እንጀራ መግቡት፥ የመከራም ውኃ አጠጡት።’ ”


“እውቀትን ለማን ያስተምረዋል? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወተትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን?”


እርሱ ከፍ ባለ ሥፍራ ይቀመጣል፤ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራም ይሰጠዋል፥ ውኃውም የማታቋርጥ ትሆናለች።


አይሞትም ወደ ጉድጓድም አይወርድም፥ እንጀራም አይጐድልበትም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements