Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 29:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በአርኤልም ላይ የሚዋጉ፥ እርሷንና ምሽግዋንም የሚወጉ የሚያስጨንቋትም፥ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት እንደ ሕልምና፥ እንደ ሌሊት ራእይ ይሆናል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 አርኤልን የሚወጋ የአሕዛብ ሁሉ መንጋ፣ በእርሷና በምሽጓ ላይ አደጋ የሚጥልና የሚከብባት፣ እንደ ሕልም በሌሊትም እንደሚታይ ራእይ ይሆናል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የእግዚአብሔር መሠዊያ የሆነችውን ከተማ ለማጥቃት የሚመጡ የመንግሥታት ሠራዊቶች ሁሉ ከነጦር መሣሪያዎቻቸው ይደመሰሳሉ፤ እንደ ሕልም ወይም በእንቅልፍ ልብ እንደሚታሰብ ነገር የተረሱ ይሆናሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በአ​ር​ኤ​ልም ላይ የሚ​ዋጉ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም የሚ​ወጉ፥ በእ​ር​ሻ​ዋም ላይ የሚ​ሰ​በ​ሰቡ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ትም፥ የአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ብል​ጽ​ግና እን​ደ​ሚ​ያ​ልም ሰው ሕልም ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በአርኤልም ላይ የሚዋጉ፥ እርስዋንና ምሽግዋንም የሚወጉ የሚያስጨንቋትም፥ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት እንደ ሕልምና እንደ ሌሊት ራእይ ይሆናል።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 29:7
17 Cross References  

እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፥ እንደ ሌሊትም ራእይ ይሰደዳል።


በዚያም ቀን በኢየሩሳሌም ላይ የሚነሡትን አሕዛብ ሁሉ ለማጥፋት እፈልጋለሁ።


በመሸ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሽብር አለ! ከመንጋቱም በፊት አንዳቸውም አይገኙም። የዘረፉን ሰዎች እድል ፈንታ፥ የበዘበዙንም ዕጣ ይህ ነው።


ከሕልም እንደሚነቃ፥ አቤቱ፥ ስትነቃ መልካቸውን ትንቃለህ።


የጌታም መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ።


አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው፤ ከምንም እንደሚያንሱ፥ እንደ ባዶ ነገር ይቈጠራሉ።


እነሆ፥ መልካም ዜና የሚያመጣ፥ ሰላምንም የሚያሰማ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ በዓሎችሽን አክብሪ፥ ስእለቶችሽን ክፈዪ፤ አጥፊው ፈጽሞ ተቆርጧልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንቺ በኩል አያልፍምና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements