Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 29:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ፦ “ይህን አንብብ” ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፦ “ማንበብ አላውቅም” ይላቸዋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ደግሞም ጥቅልሉን መጽሐፍ ማንበብ ለማይችል ሰው፣ “እባክህን አንብብልን” ብላችሁ ብትሰጡ፣ “ማንበብ አልችልም” ይላችኋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ማንበብ ወደማይችል ሰው ወስዳችሁ “አንብብልን” ብትሉት፥ “እኔ ማንበብ አልችልም” ይላችኋል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ደግ​ሞም መጽ​ሐ​ፉን ማን​በ​ብን ለማ​ያ​ውቅ፥ “ይህን አን​ብብ” ብለው በሰ​ጡት ጊዜ እርሱ፥ “ማን​በብ አላ​ው​ቅም” ይላ​ቸ​ዋል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ፦ ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፦ ማንበብ አላውቅም ይላቸዋል።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 29:12
8 Cross References  

በዚያም ቀን ደንቆሮዎች የመጽሐፍን ቃል ይሰማሉ፥ የዕውሮችም ዐይኖች ጭጋግና ጨለማው ተገፎላቸው ያያሉ።


ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ትተሃልና ለእኔ ካህን እንዳትሆን ትቼሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።


እኔም፦ “የጌታን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና እነዚህ ተሞኝተው ይህን አድርገዋል በእውነት ድሆች ናቸው፤


ምስክርነቱን አሽገው፤ ሕጉንም በደቀ መዛሙርቴ መካከል አትመው።


ይህ ሁሉ ራእይ እንደ ታተመ የመጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል፤ ማንበብንም ለሚያውቅ፦ “ይህን አንብብ” ብለው ባዘዙት ጊዜ እርሱ፦ “ታሽጓልና አልችልም” ይላቸዋል፤


ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፥ በከንፈሮቹም ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements