Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 28:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በለምለሙ ሸለቆ ራስ ላይ ያለች የረገፈች የክብሩ ጌጥ አበባ ከመከር በፊት አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች፤ያያት ሁሉ እጁን ሰዶ ይበላታል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በለምለሙ ሸለቆ ዐናት ላይ ጕብ ብላ፣ የክብሩ ውበት የሆነች ጠውላጋ አበባ፣ ከመከር በፊት እንደ ደረሰች፣ ሰውም ድንገት አይቶ እንደሚቀጥፋት ወዲያውኑም እንደሚውጣት በለስ ትሆናለች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከለምለሙ ሸለቆ በላይ ያለችው ሰማርያ በፍጥነት ክብርዋን ታጣለች፤ እርስዋም እንደሚረግፍ አበባና በበለስ ወራት መጀመሪያ በስለው በመገኘታቸው ተለቅመው እንደሚበሉ የበለስ ፍሬዎች ትሆናለች።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በረ​ዥም ተራራ ራስ ላይ ያለች የረ​ገ​ፈች የክ​ብሩ ተስፋ አበባ አስ​ቀ​ድማ እን​ደ​ም​ት​በ​ስል በለስ ትሆ​ና​ለች፤ ሰውም ባያት ጊዜ በእጁ ሳይ​ቀ​በ​ላት ይበ​ላት ዘንድ ይፈ​ጥ​ናል።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 28:4
12 Cross References  

ምሽግሽ ሁሉ የመጀመሪያውን የበሰለ ፍሬ እንደ ያዙ እንደ በለስ ዛፎች ነው፤ በሚወዛወዙ ጊዜ በሚበላው አፍ ውስጥ ይወድቃሉ።


የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም።


ፍቅራችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በማለዳም እንደሚያልፍ ጠል ነውና ኤፍሬም ሆይ! ምን ላድርግልህ? ይሁዳ ሆይ! ምን ላድርግልህ?


ለኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል ለሆነች፥ በወይን ጠጅ ለተሸነፉ፥ በለምለሙ ሸለቆአቸው ራስ ላይ ላለችም ለረገፈች ለክብሩ ጌጥ አበባ ወዮላት!


በለስም በብርቱ ነፋስ ስትናውጥ ያልበሰለ ፍሬ እንደሚረግፍ የሰማይ ከዋክብትም ወደ ምድር ወደቁ፤


በወንድሞቹ መካከል ፍሬያማ ቢሆንም እንኳ የምሥራቅ ነፋስ ይመጣል፥ የጌታ ነፋስ ከምድረበዳ ይመጣል፤ ፈሳሹንም ይጠፋል፥ ምንጩንም ይደርቃል፥ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ያሉበትን መዝገብ ይበዘብዛል።


ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ ፍርሃት ነበረ፥ በእስራኤልም መካከል ታበየ፤ ነገር ግን በኣልን በማምለክ በበደለ ጊዜ ሞተ።


ኤፍሬም ተመታ፥ ሥሩም ደረቀ፥ ፍሬም አያፈራም፤ ደግሞም ቢወልዱ እንኳ እጅግ የሚወዱአቸውን የማኅፀናቸውን ፍሬ እገድላለሁ።


ሕፃኑም፤ ‘አባባ’ ወይም ‘እማማ’ ብሎ መጥራት ከመቻሉ በፊት፤ የደማስቆ ሀብትና የሰማርያ ምርኮ በአሦር ንጉሥ ይወሰዳል።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements