ኢሳይያስ 26:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቁጣውን ሊያመጣባቸው፥ እነሆ፥ ጌታ ከስፍራው ይወጣል፤ ምድርም ያፈሰሰችውን ደም ትገልጣለች፥ የተገደሉትንም ከእንግዲህ ወዲህ አትሸሽግም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 በምድር ላይ የሚኖረውን ሕዝብ ስለ ኀጢአቱ ለመቅጣት፣ እነሆ፤ እግዚአብሔር ከመኖሪያው ወጥቶ ይመጣል፤ ምድር በላይዋ የፈሰሰውን ደም ትገልጣለች፤ የተገደሉትንም ከእንግዲህ አትሸሽግም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 በምድር ላይ የሚኖሩትን ሕዝቦች ስለ ኃጢአታቸው ለመቅጣት እግዚአብሔር ከሰማይ መኖሪያው ይገለጣል፤ በዚያን ጊዜ በምድር ላይ ተሸሽገው የሚኖሩ የነፍሰ ገዳዮች ሥራ ይጋለጣል፤ ምድርም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ታጋልጣለች። የተገደሉትንም አትደብቅም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 እነሆ፥ እግዚአብሔር በምድር በሚኖሩት ላይ ከመቅደሱ መቅሠፍቱን ያመጣል፤ ምድርም ደምዋን ትገልጣለች፤ ሙታኖችዋንም ከእንግዲህ ወዲህ አትከድንም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቍጣውን ያመጣባቸው ዘንድ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ከስፍራው ይወጣል፥ ምድርም ደምዋን ትገልጣለች፥ ሙታኖችዋንም ከእንግዲህ ወዲህ አትከድንም። See the chapter |