ኢሳይያስ 25:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 የጌታም እጅ በዚህ ተራራ ላይ ታርፋለች፤ ጭድም በጭቃ ውስጥ እንደሚረገጥ እንዲሁ ሞዓብ በሥፍራው ይረገጣል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 የእግዚአብሔር እጅ በዚህ ተራራ ላይ ያርፋል፤ ነገር ግን ጭድ ከጭቃ ጋራ እንደሚረገጥ፣ ሞዓብም እንዲሁ ይረገጣል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 የእግዚአብሔር ኀይል የጽዮንን ተራራ ይጠብቃል። የሞአብ ሕዝብ ጭድ ከጭቃ ጋር በጒድጓድ ውስጥ እንደሚረገጥ ይረገጣሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ ዕረፍትን ይሰጠናል፤ እህልም በመንኰራኵር ጭድም በጭቃ እንደሚበራይ እንዲሁ ሞዓብ ይረገጣል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 የእግዚአብሔርም እጅ በዚህ ተራራ ላይ ታርፋለች፥ ጭድም በጭቃ ውስጥ እንደሚረገጥ እንዲሁ ሞዓብ በሥፍራው ይረገጣል። See the chapter |