ኢሳይያስ 20:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ ጉስቁልና ይነዳቸዋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 እንዲሁ የአሦር ንጉሥ ወጣትና ሽማግሌ የሆኑትን የተማረኩ ግብጻውያንንና የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ዕርቃናቸውንና ባዶ እግራቸውን ይወስዳቸዋል፤ መቀመጫቸውን ገልቦ በመስደድም ግብጽን ያዋርዳል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 የአሦር ንጉሠ ነገሥት ለግብጻውያን ኀፍረት ይሆን ዘንድ መቀመጫዎቻቸው ሳይሸፈኑ ወጣቶችም ሆኑ ሽማግሌዎች ዕራቊታቸውንና ባዶ እግራቸውን ሆነው ግብጾችንና ኢትዮጵያውያንን በምርኮ ይመራቸዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብፅንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ፥ ገላቸውንም ገልጦ ለግብፅ ኀፍረት ይነዳቸዋል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ ጕስቍልና ይነዳቸዋል። See the chapter |