ኢሳይያስ 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 የያዕቆብ ቤት የሆነውን፤ ሕዝብህን ትተሃል፤ እነርሱ በምሥራቅ ሰዎች ከንቱ አምልኮ ተሞልተዋልና፤ እንደ ፍልስጥኤማውያን ያሟርታሉ፤ ከባዕዳን ጋር ተባብረዋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 የያዕቆብ ቤት የሆነውን ሕዝብህን ትተሃል፤ እነርሱ በምሥራቅ ሰዎች ከንቱ አምልኮ ተሞልተዋልና፤ እንደ ፍልስጥኤማውያን ያሟርታሉ፤ ከባዕዳን ጋራ አገና ይማታሉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 አምላክ ሆይ! የያዕቆብ ዘሮች የሆኑ ሕዝብህን እርግፍ አድርገህ ትተሃል፤ ምድሪቱ በምሥራቅ አገር ሰዎች ጥንቈላና በፍልስጥኤማውያን ሟርት ተሞልታለች፤ ሕዝቡም ከአሕዛብ ጋር ተባብረዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ሕዝቡን የያዕቆብን ቤት ትቶአልና፤ ምድራቸው እንደ ቀድሞው እንደ ፍልስጥኤማውያን ምድር በሟርት ተሞልቶአልና፤ እንደ ባዕድ ልጆችም ሆነዋልና፤ ብዙ እንግዶች ልጆችም ተወልደውላቸዋልና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ሕዝብህን የያዕቆብን ቤት ትተሃልና፥ ይኸውም የምሥራቅን ሰዎች አመል ስለ ተሞሉ፥ እንደ ፍልስጥኤማውያንም ምዋርተኞች ስለ ሆኑ፥ ከባዕድ ልጆችም ጋር ስለ ተባበሩ ነው። See the chapter |