Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 2:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የተርሴስን መርከቦች ሁሉ፤ የክብር ጀልባዎችን ሁሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የተርሴስን መርከቦች ሁሉ፣ የክብር ጀልባዎችን ሁሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እጅግ የተዋቡ ዕቃዎችንና የተርሴስ መርከቦችን እንኳ ያሰጥማል፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በባ​ሕ​ሩም መር​ከብ ሁሉ ላይ፥ በተ​ጌጡ ጣዖ​ታ​ትም ምስል ሁሉ ላይ ይሆ​ናል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በተርሴስም መርከብ ሁሉ ላይ፥ የሚያማምሩ ጣዖታትም ሁሉ ላይ ይሆናል።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 2:16
13 Cross References  

ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመት ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።


ስለ ጢሮስ የተነገረ ትንቢት። እናንተ የተርሴስ መርከቦች ሆይ፥ ወደባቹህ ፈርሷልና አልቅሱ፤ ዜናው ከኪትም ምድር ደርሷችኋል።


የመርከባቸውንም ጭነት ከእንግዲህ ወዲህ የሚገዛ የለምና የምድር ነጋዴዎች ያለቅሱላታል፤ ያዝኑላትማል፤


እርሱ አክብሮሻልና ለአምላክሽ ለጌታ ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ልጆችሽን ከሩቅ፥ ከእነርሱ ጋርም ብራቸውንና ወርቃቸውን ለማምጣት፥ ደሴቶች የተርሴስ መርከቦችም አስቀድመው ይጠባበቁኛል።


ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፥ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ።


የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤


በባሕርም ከሚኖሩ ሕይወት ካላቸው ፍጥረቶች ሲሶው ሞተ፤ የመርከቦችም ሲሶው ወደመ።


የሰው እብሪት ይዋረዳል፤ የሰውም ኩራት ይወድቃል፤ በዚያን ቀን ጌታ ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፤


እናንተ የተርሴስ መርከቦች ሆይ፥ ምሽጋችሁ ፈርሶአልና ዋይ በሉ።


በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ያዋን፥ በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።


የተርሴስ መርከቦች ሸቀጥሽን የሚያጓጉዙልሽ ነበሩ፤ አንቺም ተሞልተሽ ነበር፥ በባሕርም ልብ ውስጥ እጅግ ከበርሽ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements