Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 19:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 መስኖዎቹም ይከረፋሉ፥ የግብጽም ጅረቶች ያንሳሉ ይደርቃሉም፤ ደንገሉና ቄጠማውም ይጠወልጋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 መስኖዎቹ ይከረፋሉ፤ የግብጽ ጅረቶች ይጐድላሉ፤ ይጠፋሉም። ደንገሉና ቄጠማውም ይጠወልጋል፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ወንዞቹ ይገማሉ፤ የግብጽ መስኖ ውሃ ቀስ በቀስ እየጐደለ ይደርቃል፤ ደንገሎቹና ቀጤማዎቹ ይጠወልጋሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ወን​ዞ​ችም ይነ​ጥ​ፋሉ። ቦዮ​ችና መስ​ኖች ያን​ሳሉ፤ ይደ​ር​ቃ​ሉም፤ ደን​ገ​ልና ቄጤማ ይጠ​ወ​ል​ጋሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ወንዞቹም ይገማሉ፥ የግብጽም መስኖች ያንሳሉ ይደርቃሉም፥ ደንገልና ቄጠማ ይጠወልጋሉ።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 19:6
10 Cross References  

ቈፈርኩ ውኃም ጠጣሁ፥ የግብጽንም ወንዞች ሁሉ በእግሬ ጫማ አደረቅኩ።”


“በውኑ ደንገል ረግረግ በሌለበት መሬት ይበቅላልን? ወይስ ቄጠማ ውኃ በሌለበት ቦታ ይለመልማልን?


‘በባዕድ አገር ጉድጓድ ቆፍሬ፥ ውሃ ጠጣሁ፤ በእግሬ ኮቴዎች የግብጽን ወንዞች አድርቄአለሁ’ ብለህ ታብየሃል።


በዓባይ ወንዝ ያሉትም ዓሦች ይሞታሉ፥ የዓባይ ወንዝም ይገማል፤ ግብፃውያንም የዓባይን ወንዝ ውኃ ለመጠጣት ይጠላሉ።’”


ደግሞም ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ፥ የደንገል ሣጥን ለእርሱ ወስዳ ዝፍትና ቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም እዚያ ውስጥ አስገባችው፥ በወንዝም ዳር ባለ በቄጠማ ውስጥ አስቀመጠችው።


መልእክተኞችን በባሕር ላይ፥ የደንገል መርከቦችንም በውኃ ላይ ለምትልክ ምድር ወዮላት! እናንተ ፈጣን መልእክተኞች ሆይ፥ ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ፥ ከቅርብም ከሩቅም አስፈሪ ወደ ሆነ ሕዝብ፥ ኀያል ወደሆነና ወደሚገዛ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሂዱ።


የኔምሬም ውኆች ይደርቃሉ፤ ሣሩም ደርቋል፤ ለጋውም ጠውልጓል፤ ልምላሜውም ሁሉ የለም።


እነሆ መልካቸው ያማረ፥ ሥጋቸው የወፈረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ይበሉ ጀመር።


አንቺ በዓባይ ፈሳሾች መካከል ከተቀመጠችው፥ ውኃም በዙሪያዋ ከነበራት፥ ምሽግዋም ባሕር ከነበረ፥ ቅጥርዋም በባሕር ውስጥ ከነበረ ከኖእ አሞን ትበልጫለሽን?


ገና ሲለመልም ሳይቀጠፍም፥ ከአትክልት ሁሉ በፊት ይደርቃል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements