ኢሳይያስ 19:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ይህም ለሠራዊት ጌታ በግብጽ ምድር ምልክትና ምስክር ይሆናል፤ ከሚያስጨንቁአቸው ምክንያት ወደ ጌታ በመጮኻቸው፥ እርሱ መድኃኒትንና ኃያልን ሰዶ ያድናቸዋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ይህም በግብጽ ምድር ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ምልክትና ምስክር ይሆናል፤ ከሚያስጨንቋቸውም የተነሣ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ፣ አዳኝና ታዳጊ ይልክላቸዋል፤ እርሱም ያድናቸዋል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 እነርሱም የሠራዊት አምላክ በግብጽ ምድር ለመኖሩ ምልክትና ምስክር ይሆናሉ፤ በዚያ የሚኖሩ ሕዝቦች ችግር ሲደርስባቸው እግዚአብሔር እንዲረዳቸው በሚጠይቁበት ጊዜ የሚታደጋቸውን አዳኝ ይልክላቸዋል፤ እርሱም ከጠላቶቻቸው ያድናቸዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ይህም ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በግብፅ ምድር ለዘለዓለም ምልክት ይሆናል፤ ከሚያስጨንቋቸው የተነሣ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉና፥ እርሱም የሚያድናቸውን ሰው ይልክላቸዋል፤ ይፈርዳል፤ ያድናቸዋልም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ይህም ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በግብጽ ምድር ምልክትና ምስክር ይሆናል፥ ከሚያስጨንቁአቸው የተነሣ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉና፥ እርሱም መድኃኒትንና ኃያልን ሰድዶ ያድናቸዋልና። See the chapter |