ኢሳይያስ 16:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ስለዚህ ሞዓብ ስለ ሞዓብ ዋይታ ያሰማ፤ ሁሉም ዋይታ ያሰማሉ፤ ስለ ቂርሐራሴት መሠራት በጥልቅ ኀዘን ታለቅሳላችሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ስለዚህ ሞዓባውያን ዋይ ይላሉ፤ በአንድነትም ስለ ሞዓብ ዋይታ ያሰማሉ፤ ስለ ቂርሐራሴት ከተማ ሰዎች ትዝታ፣ በሐዘን ያለቅሳሉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ስለዚህ ሞአብ ታልቅስ፤ ሰዎችም ሁሉ ስለ ሞአብ ያልቅሱ፤ በቂርሔሬስ ከተማ የነበረው ምርጥ ምግብ ትዝ እያላቸው በታላቅ ሐዘን ያለቅሳሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ሞዓብ ዋይ በሉ፤ ሁሉም በሞዓብ ዋይ ይላሉና፤ በዴሴት የሚኖሩም አያመልጡም፤ ጠብን ያጭራሉ፤ ያፍራሉም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ስለዚህ ሞዓብ ስለ ሞዓብ ዋይ ይላል፥ ሁሉም ዋይ ይላል፥ ስለ ቂርሐራሴት መሠራት በጥልቅ ኀዘን ታለቅሳላችሁ። See the chapter |