ኢሳይያስ 16:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ምክርን ለግሺ፥ ፍትህን አስፍኚ፥ በቀትር ጊዜ ጥላሽን እንደ ሌሊት አጢይ፤ ስደተኞችን ሸሽጊ፥ የሸሹትን አሳልፈሽ አትስጪ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 “ምክር ለግሱን፤ ውሳኔ ስጡን፤ በቀትር ጥላችሁን እንደ ሌሊት አጥሉብን፤ የሸሹትን ደብቁ፤ ስደተኞችን አሳልፋችሁ አትስጡ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 የሞአብ መልእክተኞች ለይሁዳ ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “ምን ማድረግ እንደሚገባን ምከሩን፤ በቀትር ጊዜ የእናንተ ጥላ እንደ ሌሊት ጨለማ ይከልለን። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 አርኖንም በምትኖርበት ምሽግ መጠለያን ትሠራ ዘንድ ብዙ ትመክራለች፤ በቀትር ጊዜ እንደ ሌሊት ደንግጠው ይሸሻሉ፤ ወደ እናንተም አታስገቡአቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ምክርን ምከሪ፥ ፍርድን አድርጊ፥ በቀትር ጊዜ ጥላሽን እንደ ሌሊት አድርጊ፥ የተሰደዱትን ሸሽጊ፥ የሸሹትን አትግለጪ። See the chapter |