ኢሳይያስ 14:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና የመታሽ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 እናንተ ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ የመታችሁ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁ ደስ አይበላችሁ፤ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፤ ፍሬውም ተወርዋሪ መርዘኛ እባብ ይሆናል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 የፍልስጥኤም ሕዝብ ሆይ! እነሆ የተደበደባችሁበት በትር ተሰበረ፤ ሆኖም ደስ ሊላችሁ አይገባም፤ አንድ እባብ በሞተ ጊዜ ሌላ ከእርሱ የባሰ በቦታው ይተካል፤ ከእባብ ዕንቊላል በክንፍ የሚበር እሳት የመሰለ ዘንዶ ይፈለፈላል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ዘር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና፥ የኀይላችሁ ቀንበር ተሰብሮአልና ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና የመታሽ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ። See the chapter |