ኢሳይያስ 13:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 በዘመናት ሁሉ የሚቀመጥባት አይኖርም፤ የሚቀመጥባትም የለም ዐረብ በዚያ ድንኳኑን አይተክልም፤ እረኛም መንጋውን በዚያ አያሳርፍም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 በዘመናት ሁሉ የሚቀመጥባት አይኖርም፤ የሚቀመጥባትም የለም፤ ዐረብ በዚያ ድንኳኑን አይተክልም፤ እረኛም መንጋውን በዚያ አያሳርፍም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ዳግመኛ የሚኖርባትም አይገኝም፤ የበረሓ ዘላኖች የሆኑ ዐረቦችም ድንኳን አይተክሉባትም፤ እረኞችም መንጋ አያሰማሩባትም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ለዘለዓለም የሚቀመጥባት አይገኝም፤ ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ሰው አይኖርባትም፤ ዓረባውያንም በእርሷ አያልፉም፤ እረኞችም በውስጥዋ አያርፉም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ለዘላለም የሚቀመጥባት አይገኝም፥ ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ሰው አይኖርባትም፥ ዓረባውያንም ድንኳንን በዚያ አይተክሉም፥ እረኞችም መንጎቻቸውን በዚያ አያሳርፉም። See the chapter |