ኢሳይያስ 10:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላልና፤ “‘ይህን ሁሉ ያደረግሁት በክንዴ ብርታት ነው፤ ደግሞም በጥበቤ አስተዋይ ነኝና። የመንግሥታትን ድንበር አፈረስሁ፤ ሀብታቸውን ዘረፍሁ፤ ነገሥታታቸውን እንደ አንድ ኀያል ሆኜ አዋረድሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላልና፤ “ ‘ይህን ሁሉ ያደረግሁት በክንዴ ብርታት ነው፤ ደግሞም በጥበቤ አስተዋይ ነኝና። የመንግሥታትን ድንበር አፈረስሁ፤ ሀብታቸውን ዘረፍሁ፤ ነገሥታታቸውን እንደ አንድ ኀያል ሆኜ አዋረድሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 የአሦር ንጉሠ ነገሥት በመደንፋት ሲናገር እንዲህ ብሎአል፦ “ይህን ሁሉ ያደረግኹ እኔ ራሴ ነኝ፤ እኔ ብርቱ፥ ዐዋቂና ብልኅ ነኝ፤ በመንግሥታት መካከል የነበረውን ወሰን አፈራረስኩ፤ ያካበቱትንም ሀብት ሁሉ ወሰድኩ፤ በእነዚያም አገሮች የሚኖሩትን ሕዝብ ሁሉ በጀግንነቴ አዋረድኳቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 እርሱ እንዲህ ብሎአልና፥ “በኀይሌ አደርጋለሁ፤ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፤ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 እርሱ እንዲህ ብሎአልና፦ አስተዋይ ነኝና በእጄ ኃይልና በጥበቤ አደረግሁት፥ የአሕዛብን ድንበሮች አራቅሁ፥ ሀብታቸውንም ዘረፍሁ፥ እንደ ጀግናም ሆኜ በምድር የተቀመጡትን አዋረድሁ፥ See the chapter |