Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 1:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፤ ዝገትሽን ፈጽሜ አጠራለሁ፤ ጉድፍሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፤ ዝገትሽን ፈጽሜ አጠራለሁ፤ ጕድፍሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በከባድ ቊጣዬ እቀጣሻለሁ፤ ከዝገትሽ አጠራሻለሁ፤ ርኲሰትሽንም በማስወገድ አነጻሻለሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እጄ​ንም በአ​ንቺ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ አግ​ል​ሻ​ለሁ፤ ዝገ​ት​ሽ​ንም አነ​ጻ​ለሁ፤ ቆር​ቆ​ሮ​ሽ​ንም ሁሉ አስ​ወ​ግ​ዳ​ለሁ፤ ዐመ​ፀ​ኞ​ችን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ሕገ ወጦ​ች​ንም ከአ​ንቺ አስ​ወ​ግ​ዳ​ለሁ፤ ትዕ​ቢ​ተ​ኞ​ች​ንም አዋ​ር​ዳ​ለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እጄንም በአንቺ ላይ አመጣለሁ፥ ዝገትሽንም በጣም አነጻለሁ፥ ቆርቆሮሽንም ሁሉ አወጣለሁ፥

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 1:25
18 Cross References  

ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቁርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።


ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ አቀልጣቸዋለሁ እፈትናቸዋለሁም፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው ምንድነው?


ጌታ የጽዮንን ሴቶች እድፍ ያጥባል፤ ኢየሩሳሌምንም ከተነከረችበት ደም በፍርድና በሚያቃጥል መንፈስ ያነጻታል።


ብርሽ ዝጎአል፤ ምርጥ የወይን ጠጅሽ ውሃ ገባው፤


በዚያ ቀን በእኔ ላይ አምፀሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም፤ በኩራትሽ የተደሰቱትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ላይ ዳግመኛ አትታበዪም።


ብርም በማቅለጫ ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ በውስጡዋ ትቀልጣላችሁ፥ እኔም ጌታ መዓቴን እንዳፈሰስሁባችሁ ታውቃላችሁ።


ከእናንተም ዘንድ ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ። ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


ወናፉ በኃይል አናፋ እርሳሱም በእሳት ቀለጠ፤ አንጥረኛውም መልሶ በከንቱ ያቀልጠዋል ነገረ ግን ኃጢአተኞች አልተወገዱም።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ተነሣሣ፤ ንስሓም ግባ።


መንሹ በእጁ ነው፤ አውድማውንም ያጠራል፤ ስንዴውን በጎተራ ይከተዋል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


ሰው ብርንና መዳብን ብረትንና እርሳስን ቆርቆሮንም ለማቅለጥ እሳትን ሊያነድበት በማቅለጫ እንደሚሰበስብ፥ እንዲሁ በቁጣዬና በመዓቴ እሰበስባችኋለሁ፥ በዚያም ውስጥ እጨምራችኋለሁ አቀልጣችሁማለሁ።


“የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላልና፥ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ ምድሪቱንና ሕዝቡን ይክሳልና፥ እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ።”


የምድርን ኃጢአተኞች ሁሉ እንደ ርኩሰት አጠፋሃቸው፥ ስለዚህ ምስክርህን ወደድሁ።


ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፥ ይህም ኃጢአትን የማስወገድ ፍሬ ነው።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁላችሁ የብረት ዝቃጭ ሆናችኋልና፥ ስለዚህ እነሆ፥ በኢየሩሳሌም ውስጥ እሰብስባችኋለሁ።


ማደሪያህ በሽንገላ መካከል ነው፥ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ለማወቅ እንቢ ብለዋል፥ ይላል ጌታ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements