ሆሴዕ 7:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ሁሉም እንደ ምድጃ ግለዋል፥ ፈራጆቻቸውንም አጥፍተዋል፤ ነገሥታቶቻቸውም ሁሉ ወድቀዋል፤ ከእነርሱም መካከል ወደ እኔ የጮኸ የለም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤ ገዦቻቸውን ፈጁ፤ ንጉሦቻቸው ሁሉ ወደቁ፤ ከእነርሱም ወደ እኔ የቀረበ ማንም የለም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 “ሁሉም በቊጣ እንደ ምድጃ ግለው ገዢዎቻቸውን ፈጁ፤ ንጉሦቻቸውንም በየተራ አጠፉ፤ ይህም ሁሉ ሲሆን ከእነርሱ አንድ እንኳ የእኔን ርዳታ የጠየቀ የለም።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ሁሉም እንደ ምድጃ ግለዋል፤ ፈራጆቻቸውንም በሉ፤ ነገሥታቶቻቸውም ሁሉ ወደቁ፤ ከእነርሱም መካከል የሚጠራኝ የለም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ሁሉም እንደ ምድጃ ግለዋል፥ ፈራጆቻቸውንም በሉ፥ ነገሥታቶቻቸውም ሁሉ ወደቁ፥ ከእነርሱም ወደ እኔ የሚጮኽ የለም። See the chapter |