ሆሴዕ 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 አለበለዚያ ዕራቁትዋን እንድትሆን እገፍፋታለሁ፥ እንደ ተወለደችበትም ቀን አደርጋታለሁ፥ እንደ ምድረ በዳና እንደ ደረቅ ምድር አደርጋታለሁ፥ በጥምም እገድላታለሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 እናታቸው አመንዝራ ናት፤ በውርደትም ፀንሳቸዋለች፤ እርሷም፣ ‘እንጀራዬንና ውሃዬን ይሰጡኛል፤ ሱፌንና የሐር ልብሴን፣ ዘይቴንና መጠጤን ይሰጡኛል፤ ስለዚህ ውሽሞቼን ተከትዬ እሄዳለሁ’ አለች። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 እናታቸው አመንዝራ ስለ ሆነች እነርሱን ባሳፋሪ መንገድ ፀንሳቸዋለች፤ እርስዋም ይህን ያደረገችው ምግቤንና ውሃዬን፥ የሱፍና የተልባ እግር ልብሴን፥ ዘይቴንና መጠጤን የሚሰጡኝ ስለ ሆነ ፍቅረኞቼን ተከትዬ እሄዳለሁ ብላ ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እናታቸው አመንዝራለችና፤ የወለደቻቸውም፥ “እንጀራዬንና ውኃዬን፥ ቀሚሴንና መደረቢያዬን፥ ዘይቴንና የሚገባኝን ሁሉ የሚሰጡኝ ወዳጆችን እከተላቸው ዘንድ እሄዳለሁ” ብላለችና አሳፈረቻቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ዕራቁትዋን እንዳልገፍፋት፥ እንደ ተወለደችበትም ቀን እንዳላደርጋት፥ እንደ ምድረ በዳና እንደ ደረቅ ምድር እንዳላደርጋት፥ See the chapter |