Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሆሴዕ 14:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ለእስራኤልም እንደ ጠል እሆነዋለሁ፤ እንደ አበባም ያብባል፥ እንደ ሊባኖስም ሥሮቹን ይሰድዳል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ቅርንጫፉ ያድጋል፤ ውበቱ እንደ ወይራ ዛፍ፣ ሽታውም እንደ ሊባኖስ ዝግባ ይሆናል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ቡቃያዎቻቸው ይለመልማሉ፤ እንደ ወይራ ዛፍ የሚያምሩ ይሆናሉ፤ እንደ ሊባኖስ ደን መልካም መዓዛ ይሰጣሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እንደ ጠል እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ እንደ አበ​ባም ያብ​ባል፥ እንደ ሊባ​ኖ​ስም ሥሩን ይሰ​ድ​ዳል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ቅርንጫፎቹም ይዘረጋሉ፥ ውበቱም እንደ ወይራ፥ ሽታውም እንደ ሊባኖስ ይሆናል።

See the chapter Copy




ሆሴዕ 14:6
19 Cross References  

ጻድቃን አይተው ይፈራሉ፥ በእርሱም ይሥቃሉ እንዲህም ይላሉ፦


ነገር ግን የሚያስፈልገኝን ሁሉ ተቀብያለሁ፤ ተትረፍርፎልኛልም፤ መዓዛው ያማረ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከኤጳፍሮዲጡስ ተቀብዬ በሁሉ ተሟልቶልኛል።


“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።


ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው፤ እንዲህም ሲል ነገራቸው “መንግሥተ ሰማያት አንድ ሰው ወስዶ በእርሻው የዘራትን የሰናፍጭ ዘር ትመስላለች፤


ጌታ ስምሽን፦ “በመልካም ፍሬ የተዋበች የለመለመች የወይራ ዛፍ” ብሎ ጠራው፤ በጽኑ ዐውሎ ነፋስ ጩኸት እሳትን አነደደባት፥ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል።


ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፥ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።


ወደ እርሱም ቀረበ፥ ሳመውም፥ የልብሱንም ሽታ አሸተተ፥ ባረከውም፥ እንዲህም አለ፦ “የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው እርሻ ሽታ ነው፥


ዓይኔም ጠላቶቼን ቃኘች፥ ጆሮዬም በእኔ ላይ የተነሡትን ክፉዎች ሰማች።


በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያቈጠቁጣል፥ ያብባልም፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።


እጅግ ያብባል በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር፥ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፤ የጌታንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።


ታያላችሁ፥ ልባችሁም ሐሤት ታደርጋለች፥ አጥንታችሁም እንደ ለምለም ሣር ትበቅላለች፤ የጌታም እጅ ለሚፈሩት ትታወቃለች፥ በጠላቶቹም ላይ ይቈጣል።


እኛም እንወቅ፤ ጌታን ለማወቅ እንትጋ፤ እንደ ንጋትም መገለጡ እርግጥ ነው፤ እንደ ዝናብ ምድርንም እንደሚያጠጣ እንደ በልግ ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements