ሆሴዕ 10:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 እስራኤል ፍሬውን የሚሰጥ የተትረፈረፈ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያዎችን አብዝቶአል፤ እንደ ምድሩም ብልጥግና መጠን ሐውልቶችን እያሳመሩ ሠርተዋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 እስራኤል የተንዠረገገ ወይን ነበር፤ ብዙ ፍሬም አፈራ፤ ፍሬው በበዛ መጠን፣ ብዙ መሠዊያዎችን ሠራ፤ ምድሩ በበለጸገ መጠን፣ የጣዖታት ማምለኪያ ዐምዶችን አስጌጠ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 የእስራኤል ሕዝብ ብዙ ዘለላ እንደ ያዘ የወይን ተክል ናቸው፤ ፍሬ በበዛላቸው መጠን ብዙ የጣዖት መሠዊያዎችን ሠሩ፤ ምድራቸው ፍሬያማ ሆና በበለጸገችላቸው መጠን የጣዖት መስገጃ ዐምዶችን አስጊጠው ሠሩ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 እስራኤል ፍሬው የበዛለት የለመለመ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያዉን አብዝቶአል፤ እንደ ምድሩም ማማር መጠን ሐውልቶችን ሠርተዋል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 እስራኤል ፍሬው የበዛለት የለመለመ ወይን ነው፥ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያውን አብዝቶአል፥ እንደ ምድሩም ማማር መጠን ሐውልቶችን እያሳመሩ ሠርተዋል። See the chapter |