ዕብራውያን 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ቤትን የሚሠራው ከቤቱ ይልቅ የሚበልጥ ክብር እንዳለው ሁሉ፥ እንዲሁ እርሱ ከሙሴ ይልቅ የሚበልጥ ክብር የተገባው ሆኖ ተቆጥሮአልና። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ቤትን የሚሠራ ከቤቱ ይልቅ የሚበልጥ ክብር እንዳለው፣ ኢየሱስም ከሙሴ የሚበልጥ ክብር የተገባው ሆኖ ተገኝቷል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ቤትን የሚሠራ ከቤቱ ይልቅ የበለጠ ክብር እንዳለው ሁሉ ኢየሱስም ከሙሴ ይልቅ የበለጠ ክብር ይገባዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ነገር ግን የባለቤት ክብሩ ከቤቱ እንደሚበልጥ፥ ክብሩ ከሙሴ ክብር ይልቅ እጅግ ይበልጣል፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ቤትን የሚያዘጋጀው ከቤቱ ይልቅ የሚበልጥ ክብር እንዳለው መጠን፥ እንዲሁ እርሱ ከሙሴ ይልቅ የሚበልጥ ክብር የተገባው ሆኖ ተቆጥሮአልና። See the chapter |