Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዕብራውያን 12:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ምክንያቱም “እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ ተወግሮ ይሙት፤” የምትለውን ትእዛዝ መሸከም አልቻሉም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ምክንያቱም “እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ፣ በድንጋይ ተወግሮ ይሙት” የሚለውን ትእዛዝ መሸከም አልቻሉም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ በድንጋይ ተወግሮ ይሙት” የሚለው ትእዛዝ ስለ ከበደባቸው ሊሸከሙት አልቻሉም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የተ​ነ​ጋ​ገ​ራ​ቸ​ውን ሊሰ​ሙት አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ርና፥ “እን​ስ​ሳም ያን ተራራ ቢቀ​ር​በው በድ​ን​ጋይ ይወ​ግ​ሩት” ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ ተወግሮ ይሙት የምትለውን ትእዛዝ ሊታገሡ አልቻሉምና፤

See the chapter Copy




ዕብራውያን 12:20
6 Cross References  

ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ ከርግማን በታች ናቸው፤ “በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ይሁን፤” ተብሎ ተጽፎአልና።


ለእግዚአብሔር እንድኖር በሕግ በኩል ለሕግ ሞቼአለሁ፤ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ።


እንዲህም አለ፦ “ጌታ ከሲና ተራራ መጣ፥ በሴይርም እንደ ንጋት ተገለጠ፥ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥ በስተቀኙም ከእሳት ነበልባል ጋር፥ ከአእላፋት ቅዱሳኑም ጋር መጣ።


እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን ማለዳ ነጎድጓድ፥ መብረቅና ከባድ ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩ የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements