ዕብራውያን 12:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ወደ መለከት ድምፅ፥ ወይም ቃልን ወደሚያሰማ ድምጽ አልመጣችሁም። ያን ነገር የሰሙት ሁሉ ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው እስኪለምኑ አደረሳቸው፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ወደ መለከት ድምፅ ወይም ቃልን ወደሚያሰማ ድምፅ አልመጣችሁም፤ የሰሙትም ሌላ ቃል ተጨምሮ እንዳይናገራቸው ለመኑ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 የእምቢልታ ድምፅ ወይም የሚነገረው ቃል ወደሚሰማበትም አልደረሳችሁም፤ ያንን ቃል የሰሙ ሰዎች “ከእንግዲህ ወዲህ ሌላ ቃል አይነገረን” በማለት እስከ መለመን ደርሰዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ወደ መለከት ድምፅም፥ ወደ ቃሎችም ነገር አልደረሳችሁምና፥ ያንም ነገር የሰሙት ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው ለመኑ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ያንም ነገር የሰሙት ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው ለመኑ፤ See the chapter |