Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዕብራውያን 11:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፤ ጽድቅን አደረጉ፤ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፤ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 እነዚህ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፤ በቅን ፈረዱ፤ የተሰጠውን የተስፋ ቃል ተቀበሉ፤ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፤ በፍትሕ አስተዳደሩ፤ የተሰጣቸውንም ተስፋ አገኙ፤ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 እነ​ርሱ በእ​ም​ነት ተጋ​ደሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ትን ድል ነሡ፤ ጽድ​ቅን አደ​ረጉ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ውን አገኙ፤ የአ​ና​ብ​ስ​ት​ንም አፍ ዘጉ ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥

See the chapter Copy




ዕብራውያን 11:33
26 Cross References  

የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ ጽናት ያስፈልጋችኋል።


የተስፋውም ቃል የተነገረው ለአብርሃምና ለዘሩ ነበር። ለብዙዎች እንደሆነ “ለዘሮችህ” አይልም፤ ነገር ግን ለአንድ እንደሆነ “ለዘርህም” ይላል፤ እርሱም ክርስቶስ ነው።


በመጠን ኑሩ፤ ንቁም! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ዙሪያውን ይንጐራደዳል።


አብርሃም በተፈተነ ጊዜ ይስሐቅን በእምነት አቀረበ፤ የተስፋን ቃል የተቀበለው እርሱም አንድ ልጁን ሊሠዋ ዝግጁ ነበር፤


ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ከእኔ ጎን ጌታ ቆመ አበረታኝም፤ ከአንበሳም አፍ ዳንሁ።


ለነገሥታት መድኃኒትን የሚሰጥ፥ ባርያውን ዳዊትን ከክፉ ሰይፍ የሚያድነው እርሱ ነው።


በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፥ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።


ኤሁድ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ።


እነርሱም፥ “አላታለልኸንም ወይም ግፍ አልሠራህብንም፤ ከማንም እጅ አንዳች ነገር አልተቀበልህም” ብለው መለሱለት።


ስለዚህ ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለሕዝቡም ሁሉ ትክክለኛ ፍርድ አሰፈነላቸው።


እንግዲህ በርታ፤ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች በጀግንነት እንዋጋ፤ ጌታም በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ።”


ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።”


ነገር ግን አንድ ሰው “አንተ እምነት አለህ፤ እኔ ሥራ አለኝ” ቢል፤ እምነትህን ከሥራ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ።


በአህያው ላይ ተቀምጦ ሄደ፤ የነቢዩንም ሬሳ አህያውና አንበሳው እስከ አሁን በአጠገቡ እንደ ቆሙ በመንገድ ላይ ተጋድሞ አገኘው። አንበሳውም የነቢዩን ሬሳ አልበላም፤ በአህያውም ላይ አደጋ አልጣለበትም ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements