ዕንባቆም 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 በእርግጥ ወይን አታላይ ነው፤ ትዕቢተኛ ሰው በስፍራው አርፎ አይቀመጥም፤ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፤ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 በርግጥ የወይን ጠጅ አታልሎታል፤ ትዕቢተኛ ነው፤ ከቶ አያርፍም፤ እንደ መቃብር ስስታም ነው፣ እንደ ሞት ከቶ አይጠግብም፤ ሕዝቦችን ለራሱ ይሰበስባል፤ ሰዎችንም ሁሉ ማርኮ ይወስዳል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 በእርግጥ ሀብት ሰውን ያታልላል፤ ትምክሕተኛ ሰው ዕረፍት የለውም፤ እንደ መቃብር ስስታም እንደ ሞትም በቃኝ የማይል ስለ ሆነ መንግሥታትን ሁሉ ለራሱ ይወራል፤ ሕዝቦችንም ይማርካል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እርሱ አታላይና ኵሩ ሰው ነው፣ በስፍራው ዐርፎ አይቀመጥም፣ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፣ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 እርሱ አታላይና ኵሩ ሰው ነው፥ በስፍራው ዐርፎ አይቀመጥም፥ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፥ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል። See the chapter |