ዕንባቆም 1:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ጌታ አምላኬ፥ ቅዱሴ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፤ ጌታ ሆይ፥ ለፍርድ ወስነሃቸዋል፥ ዓለት ሆይ ለተግሣጽም መሠረትሃቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከቀድሞው ያለህ አይደለህምን? የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ አትሞትም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲፈርድ ሾመኸዋል፤ ዐለት ሆይ፤ ይቀጣ ዘንድ ሥልጣን ሰጥተኸዋል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! አንተ ከጥንት ጀምሮ የነበርክ ቅዱስ ነህ፤ አንተ ስለምትጠብቀን አንሞትም፥ እነርሱ ፍርድህን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መድበሃቸዋል፤ አምባችን ሆይ! እኛን እንዲቀጡ ለእነርሱ ሥልጣን ሰጥተሃቸዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፣ አቤቱ፥ ለፍርድ ሠርተኸዋል፥ ለተግሣጽም አድርገኸዋል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፥ አቤቱ፥ ለፍርድ ሠርተኸዋል፥ ለተግሣጽም አድርገኸዋል። See the chapter |