Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 9:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እንዲህም ሲል እግዚአብሔር ተናገረ፦ “በእኔና በእናንተ፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ፍጥረት ሁሉ መካከል፥ ለዘለዓለም የማደርገው፥ የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “በእኔና በእናንተ መካከል፣ ከእናንተም ጋራ ካሉ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ጋራ ከሚመጣውም ትውልድ ሁሉ ጋራ፣ የማደርገው የኪዳኑ ምልክት ይህ ነው፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ “ከእናንተና ከሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ጋር ለምገባው ለዚህ ለዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ምልክት ይሆን ዘንድ፥

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለኖኅ አለው፥ “በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል፥ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ባለው በሕ​ያው ነፍስ ሁሉ መካ​ከል፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትው​ልድ የማ​ደ​ር​ገው የቃል ኪዳኔ ምል​ክት ይህ ነው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እግዚአብሔርም አለ፤ በእኔና በእናንተ መካከላ፤ ከእናንትም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል፥ ለዘላለም የማደርገው የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 9:12
8 Cross References  

የቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ፥ በእኔና በእናንተ መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል።


ደሙም በምትኖሩባቸው ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፤ እኔም የግብጽን ምድር በመታሁ ጊዜ መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም።


ጌታ በብርቱ እጅ ከግብጽ አውጥቶናልና በእጅህ እንደ ምልክት፥ በዐይኖችህም መካከል እንደ ተንጠለጠለ ነገር ይሁንልህ።


እግዚአብሔርም ኖኅን፦ “ይህ በእኔና በምድር ላይ በሚኖሩ ሕይወት ባላቸው ፍጥረቶች መካከል ያቆምሁት የቃል ኪዳን ምልክት ነው” አለው።


አሁንም፥ እባካችሁ፥ በጌታ ማሉልኝ፥ በእውነትም ምልክት ስጡኝ፥ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንደሠራሁ እናንተ ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት ሥሩ፥


ቀስቴን በደመና አደርጋለሁ፥ ይህም በእኔና በምድር መካከል የቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements