Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 50:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ዮሴፍም አገልጋዮቹ የሆኑትን መድኃኒት ቀማሚዎች የአባቱን ሬሳ መልካም መዓዛ ባለው ሽቶ እያሹ እንዲያደርቁት ትእዛዝ ሰጠ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከዚያም ዮሴፍ የአባቱ የእስራኤል ሬሳ እንዳይፈርስ ባለመድኀኒት የሆኑ አገልጋዮቹ በመድኀኒት እንዲቀቡት አዘዘ። ባለመድኀኒቶቹም እንዳይፈርስ ሬሳውን በመድኀኒት ቀቡት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አገልጋዮቹ የሆኑትን መድኃኒት ቀማሚዎች የአባቱን ሬሳ መልካም መዓዛ ባለው ሽቶ እያሹ እንዲያደርቁት ትእዛዝ ሰጠ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ዮሴ​ፍም ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶች አገ​ል​ጋ​ዮቹ አባ​ቱን በሽቱ ያሹት ዘንድ አዘዘ፤ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶ​ችም እስ​ራ​ኤ​ልን በሽቱ አሹት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ዮሴፍም ባለመድኃኒቶች አገልጋዮች አባቱን በሽቱ ያሹት ዘንድ አዘዘ ባለመድኃኒቶችም እስራኤልን በሽቱ አሹት።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 50:2
10 Cross References  

ለእርሱም ለራሱ በሠራው መቃብር በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ በቀማሚ ብልሃት የተሰናዳ ልዩ ልዩ መልካም ሽቶ በተሞላው አልጋ ላይም አኖሩት፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የመቃብር ወግ አደረጉለት።


ዮሴፍም ዕድሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሞላው ሞተ፤ በሽቶም አሹት፥ በግብጽ ምድር በሣጥን ውስጥ አኖሩት።


ሰንበት ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም፥ የያዕቆብ እናት ማርያምና ሰሎሜ ሄደው የኢየሱስን ሥጋ ለመቀባት ሽቱ ገዙ።


እርሷ ይህን ሽቶ በሰውነቴ ላይ በማፍሰስ ለቀብሬ አደረገችው።


ኢየሱስም “ለምቀበርበት ቀን እንድትጠብቀው ተውአት፤


ነገር ግን ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን እጅግ ማልደው፥ ያዘጋጁትን ሽቱ ይዘው ወደ መቃብሩ መጡ።


እርሷ ማድረግ የምትችለውን ያህል አድርጋለች፤ ለመቃብሬ እንዲሆን ሰውነቴን አስቀድማ ቀብታለች።


ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፥ ዔሳውም በልቡ አለ፦ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል፥ ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”


ዮሴፍም በአባቱ ፊት ወደቀ፥ በእርሱም ላይ አለቀሰ፥ ሳመውም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements