Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 49:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ቁጣቸው ርጉም ይሁን፥ ጽኑ ነበርና፥ ኩርፍታቸውም፥ ብርቱ ነበርና፥ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እጅግ አስፈሪ የሆነ ቍጣቸው፣ ጭከና የተሞላ ንዴታቸው የተረገመ ይሁን፤ በያዕቆብ እበትናቸዋለሁ፤ በመላው እስራኤልም አሠራጫቸዋለሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እጅግ አስፈሪ የሆነ ቊጣቸው፥ እጅግ ጨካኝ የሆነ መዓታቸው፥ የተረገመ ይሁን። በእስራኤል ምድር ሁሉ እበታትናቸዋለሁ፤ በሕዝቡም መካከል እከፋፍላቸዋለሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ቍጣ​ቸው ርጉም ይሁን፤ ጽኑ ነበ​ርና፤ ኵር​ፍ​ታ​ቸ​ውም ብርቱ ነበ​ርና፤ በያ​ዕ​ቆብ እከ​ፋ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እበ​ታ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ቍጣቸው ርጉም ይሁን ጽኑ ነበርና ኵርፍታቸውም ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 49:7
11 Cross References  

ድንጋይ ከባድ ነው አሸዋም እንዲሁ፥ ከሁለቱ ግን የሞኝ ቁጣ ይከብዳል።


ከይሁዳም ልጆች ነገድ፥ ከስምዖንም ልጆች ነገድ፥ ከብንያምም ልጆች ነገድ፥ እነዚህን በስማቸው የተጠሩትን ከተሞች በዕጣ ሰጡ።


ከዚያም በኋላ አምኖን ፈጽሞ ጠላት፥ አስቀድሞም ሲወዳት ከነበረው ፍቅሩ ይልቅ በኋላ የጠላት ጥላቻ አየለ። አምኖንም፥ “ተነሽ ውጭልኝ!” አላት።


ከእስራኤል ልጆች ርስት ለሌዋውያን የምትሰጡአቸውን ከተሞች እንዲሁ ስጡ፤ ከብዙዎቹ ብዙ፥ ከጥቂቶቹ ጥቂት ትወስዳላችሁ፤ እያንዳንዱ እንደ ወረሱት እንደ ርስታቸው መጠን ከከተሞቻቸው ለሌዋውያን ይሰጣሉ።”


ቁጡ ሰው ክርክርን ያነሣሣል። ወፈፍተኛ ሰውም ኃጢአትን ያበዛል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements