Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 47:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውንና ፍየሎቻቸውን ከብቶቻቸውንና ሌላም ያላቸውን ነገር ሁሉ ይዘው ከከነዓን ወደዚህ መጥተዋል፤ አሁንም በጌሴም ምድር ይገኛሉ” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ፣ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው ከከነዓን አገር መጥተው በጌሤም ሰፍረዋል” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውንና ፍየሎቻቸውን ከብቶቻቸውንና ሌላም ያላቸውን ነገር ሁሉ ይዘው ከከነዓን ወደዚህ መጥተዋል፤ አሁንም በጌሴም ምድር ይገኛሉ” አለው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዮሴ​ፍም ገባ፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “አባ​ቴና ወን​ድ​ሞች በጎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ላሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ ያላ​ቸ​ውም ሁሉ ከከ​ነ​ዓን ምድር መጡ፤ እነ​ር​ሱም እነሆ፥ ወደ ጌሤም ምድር ደረሱ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ዮሴፍም ገባ ለፈርዖንም ነገረው እንዲህ ብሎ፦ አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውም ላሞቻቸውም ያላቸውም ሁሉ ከከነዓን ምድር ወጡ እነርሱም እነሆ በጌሤም ምድር ናቸው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 47:1
8 Cross References  

ዮሴፍም ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ “እኔ መጥቼ ለፈርዖን፦ ‘እንግዲህ በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤት ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል፥


አንተና ልጆችህ የልጆችህም ልጆች፥ በጎችህና ላሞችህ ከብትህም ሁሉ፥ ከእኔም በቅርበት፥ በጌሤምም ምድር ትቀመጣለህ።


በጌሴም ምድር እንዲቀበለው ያዕቆብ ይሁዳን ወደ ዮሴፍ አስቀድሞ ላከው፤ ወደ ጌሤም ምድርም ደረሱ።


የሚቀድሰውና በእርሱም የተቀደሱት ሁሉ መገኛቸው ከአንድ ነውና፤ ከዚህ የተነሣ ወንድሞች ብሎ ሲጠራቸው አያፍርም፤


የእስራኤል ልጆች በነበሩባት በጎሼን ምድር ብቻ በረዶ አልነበረም።


ሙሴም፦ “እንዲህ ማድረግ ተገቢ አይደለም ለጌታ አምላካችን የግብፃውያንን ርኩሰት እንሰዋለንና፤ እነሆ እኛ የግብፃውያንን ርኩሰት በፊታቸው ብንሠዋ በድንጋይ አይወግሩንምን?


በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብጽ ሰዎች ርኩስ ነውና፥ በጌሤም እንድትቀመጡ፦ ‘እኛ አገልጋዮችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ፥ እኛም አባቶቻችንም፥ እንስሳ አርቢዎች ነን’ በሉት።”


በፈርዖንም ቤት፥ “የዮሴፍ ወንድሞች መጡ ተብሎ ወሬ ተሰማ፥” በሰሙትም ነገር ፈርዖንና አገልጋዮቹ ደስ ተሰኙበት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements