ዘፍጥረት 45:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 እንዲህም ብለው ነገሩት፦ “ዮሴፍ ገና በሕይወቱ አለ፥ እርሱም በግብጽ ምድር ላይ ሁሉ ገዥ ሆኖአል።” ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ፥ ሊያምናቸውም አልቻለም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 አባታቸውንም፣ “እነሆ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በግብጽ ምድር ሁሉ ገዥ ሆኗል” ብለው ነገሩት። ያዕቆብም በድንጋጤ ክው አለ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 እዚያም እንደ ደረሱ አባታቸውን “ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በመላው ግብጽ ላይ አስተዳዳሪ ሆኖአል” አሉት። ያዕቆብ ግን እጅግ ደነገጠ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 እንዲህም ብለው ነገሩት፥ “ልጅህ ዮሴፍ በሕይወቱ ነው፤ እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖአል።” ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ፤ አላመናቸውምም፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 እንዲህም ብለው ነገሩት፦ ዮሴፍ ገና በሕይወት ነው እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖአል። ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ አላመናቸውም ነበርና። See the chapter |