ዘፍጥረት 44:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 እኔ አገልጋይ፥ ‘ልጅህን መልሼ ሳላመጣ ብቀር፥ ለዘለዓለም በደለኛ አድርገህ ቁጠረኝ’ በማለት፥ ስለ ልጁ ደኅንነት በአባቴ ፊት ራሴን ዋስ አድርጌአለሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 እኔ አገልጋይህ፣ ‘ልጅህን መልሼ ሳላመጣ ብቀር፣ ለዘላለም በደለኛ አድርገህ ቍጠረኝ’ በማለት፣ ስለ ልጁ ደኅንነት በአባቴ ፊት ራሴን ዋስ አድርጌአለሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ከዚህም በላይ ስለ ልጁ ደኅንነት ራሴን ዋስ አድርጌ ለአባቴ ሰጥቼአለሁ፤ ደግሞም ‘ልጁን በደኅና መልሼ ባላመጣው በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ተወቃሽ ልሁን’ ብዬ ቃል ገብቼለታለሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 እኔ አገልጋይህ በአባቴ ዘንድ ስለ ብላቴናው እንዲህ ብዬ ተውሼአለሁና፦ እርሱንስ ወደ አንተ መልሼ በፊትህ ባላቆመው በአባቴ ዘንድ በዘመናት ሁሉ ኀጢአተኛ እሆናለሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 እኔ ባሪያህ በአባቴ ዘንድ ስለ ብላቴናው እንዲህ ብዮ ተውሼአለሁና፦ እርሱንስ ወደ አንተ ባለመጣው በአባቴ ሀዘኔ በዘመናት ሁሉ ኃጢአተኛ እሆናለሁ። See the chapter |