Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 43:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ይሁዳም አባቱን እስራኤልን እንዲህ አለው “ልጁን ከእኔ ጋር ስደደው፤ እኛም በቶሎ እንሂድ፤ ይህ ከሆነ፥ አንተም፥ እኛም፥ ልጆቻችንም አንሞትም፤ እንተርፋለን።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ይሁዳም አባቱን እስራኤልን እንዲህ አለው “ልጁን ከእኔ ጋራ ስደደው፤ እኛም በቶሎ እንሂድ፤ ይህ ከሆነ፣ አንተም፣ እኛም፣ ልጆቻችንም አንሞትም፤ እንተርፋለን።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ይሁዳም አባቱን እንዲህ አለ፤ “ልጁን በእኔ ኀላፊነት አብሮን እንዲሄድ አድርግ፥ ሳንዘገይ አሁኑኑ ጒዞ እንጀምር፤ ይህ ከሆነ፥ እኛም አንተም ልጆቻችንም ሁሉ በራብ ከመሞት እንድናለን።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ይሁ​ዳም አባ​ቱን እስ​ራ​ኤ​ልን አለው፥ “እኛና አንተ ልጆ​ቻ​ች​ንም ደግሞ እን​ድ​ን​ድን፥ እን​ዳ​ን​ሞ​ትም ብላ​ቴ​ና​ውን ከእኔ ጋር ላከው፤ እኛም ተነ​ሥ​ተን እን​ሄ​ዳ​ለን።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ይሁዳም አባቱን እስራኤልን አለው፦ እኛና አንተ ልጆቻችንም ደግሞ እንድንድን እንዳንሞትም ብላቴናውን ከእኔ ጋር ስደደው እናም ተንሥተን እንሄዳለን።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 43:8
14 Cross References  

በግብጽ እህል መኖሩን ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ከመሞት መሰንበት ይሻላልና ወደዚያው ወርዳችሁ እህል ሸምቱልን” አላቸው።


“ሮቤል በሕይወት ይኑር፥ አይሙት፥ ሰዎቹም በቍጥር አይነሱ።”


አልሞትም፥ በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፥ የጌታንም ሥራ እናገራለሁ።


በአምላካችን ፊት ራሳችንን ዝቅ እንድናደርግ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንድንለምን በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ።


ከባለሟሎቹም አንዱ “በዚህች ከተማ ውስጥ የተረፈው ሕዝብ ከዚህ በፊት እንደ ሞቱት ሰዎች ሁሉ ከሞት የሚያመልጥ አይደለም፤ ስለዚህ የሆነውን ነገር ማወቅ እንድንችል ጥቂት ሰዎችን መርጠን ከሞት ከተረፉት አምስት ፈረሶች ጋር እንላክ” ሲል ሐሳብ አቀረበ።


ወደ ከተማይቱ መግባት ምንም ጥቅም የለውም፤ እዚያ ከገባን በራብ እንሞታለን፤ እዚህም ብንቀር ከመሞት አንድንም፤ ስለዚህ ተነሥተን ወደ ሶርያውያን ሰፈር እንሂድ፤ እነርሱም ቢሆኑ ከመግደል የከፋ ሌላ ምንም ነገር ሊያደርጉብን አይችሉም፤ ምናልባትም ሕይወታችንን ያተርፉ ይሆናል።”


ነገር ግን ምርኮኛ ይሆናሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን እነርሱን ወደ ምድሪቱ አስገባቸዋለሁ፥ እናንተም የናቃችኋትን ምድር ያውቋታል።


“ጌታ አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፥ አባትህንና እናትህን አክብር።


አሁንም አትፍሩ፥ እኔ እናንተንና ልጆቻችሁን እመግባችኋለሁ።” አጽናናቸውም ደስ አሰኛቸውም።


የዮሴፍም ቤተሰቦች ሁሉ፥ ወንድሞቹም የአባቱም ቤተሰቦች ወጡ፥ ልጆቻቸውንና በጎቻቸውን ከብቶቻቸውን ብቻ በጌሤም ተዉ።


አንተም ወንድሞችህን፦ እንዲህ አድርጉ በላቸው፥ ከግብጽ ምድር ለሕፃናቶቻችሁ ለሴቶቻችሁም ሰረገሎችን ውሰዱ፥ አባታችሁንም ይዛችሁ ኑ፥


‘መሄድ አንችልም፤ መሄድ የምንችለው ታናሽ ወንድማችን አብሮን ሲሄድ ብቻ ነው። ታናሽ ወንድማችንን ይዘን ካልሄድን በስተቀር፥ የሰውየውን ፊት ማየት አንችልም’ አልነው።


ያዕቆብም፥ “ልጄ አብሮአችሁ ወደዚያ አይወርድም፤ ወንድሙ እንደሆን ሞቷል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው። ይዛችሁት ስትሄዱ በመንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበት፥ ሽበቴን በመሪር ኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ” አላቸው።


እኛም፥ ‘አዎን፥ ሽማግሌ አባት አለን፤ አባታችንም በስተርጅና የወለደው ትንሽ ልጅ አለው፤ ወንድምየው ሞቷል፤ ከአንድ እናት ከተወለዱት ልጆች መካከል የተረፈው እርሱ ብቻ ነው፤ አባቱም በጣም ይወደዋል’ ብለንህ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements