Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 43:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት፤ ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ግብፃውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር አብሮ መመገብን እንደ ጸያፍ ይቈጥሩት ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት፤ ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከርሱ ጋራ ለሚበሉት ግብጻውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብጻውያን ከዕብራውያን ጋራ ዐብሮ መመገብን እንደ ጸያፍ ይቈጥሩት ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ግብጻውያን ከዕብራውያን ጋር አብሮ መመገብን እንደ ጸያፍ ይቈጥሩት ስለ ነበር ለዮሴፍ ብቻውን አንድ ገበታ፥ ለወንድማማቾቹ ሌላ ገበታ፥ እዚያ ይመገቡ ለነበሩ ግብጻውያንም ሌላ ገበታ ተዘጋጀ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ለእ​ር​ሱም ለብ​ቻው አቀ​ረቡ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ለብ​ቻ​ቸው፤ ከእ​ርሱ ጋር ለሚ​በ​ሉት ለግ​ብፅ ሰዎ​ችም ለብ​ቻ​ቸው፤ የግ​ብፅ ሰዎች ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ጋር መብ​ላት አይ​ች​ሉ​ምና፥ ይህ ለግ​ብፅ ሰዎች እንደ መር​ከስ ነውና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ለእርሱም ለብቻው አቀረቡ ለእነርሱም ለብቻቸው ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ለግብፅ ሰዎችም ለብቻቸው የግብፅ ሰዎች ከዕብራውያን ጋር መብላት አይሆንላቸውምና ይህ ለግብፅ ሰዎች እንደ መርከስ ነውና።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 43:32
4 Cross References  

ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ወጣ፥ ወደ ጌታም ጸለየ።


በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብጽ ሰዎች ርኩስ ነውና፥ በጌሤም እንድትቀመጡ፦ ‘እኛ አገልጋዮችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ፥ እኛም አባቶቻችንም፥ እንስሳ አርቢዎች ነን’ በሉት።”


ዮሴፍ ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ፥ “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ይዘሃቸው ሂድ፤ ዛሬ ቀትር ላይ አብረውኝ ስለሚበሉ ፍሪዳ ተጥሎ ምሳ ይዘጋጅ” አለው።


ያዕቆብም በተራራው ላይ መሥዋዕትን አቀረበ፥ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጠራ፥ እነርሱም ምግብ ተመገቡ፥ በዚያም በተራራ ሌሊቱን ሙሉ አሳለፉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements