Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 42:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ነገር ግን ታናሽ ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡት። በዚያንም ጊዜ ታማኝ ሰዎች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ እናንተም በምድሪቱ እንደ ልብ ለመዘዋወር ትችላላችሁ።’”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ነገር ግን ታናሽ ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡት። በዚያም ጊዜ ታማኝ ሰዎች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ እናንተም በምድሪቱ እንደ ልብ ለመዘዋወር ትችላላችሁ።’ ”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ታናሽ ወንድማችሁንም ይዛችሁልኝ ኑ፤ በዚህ ዐይነት ታማኞች ሰዎች መሆናችሁንና ሰላዮችም አለመሆናችሁን አረጋግጣለሁ፤ ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ በዚህም አገር ቈይታችሁ እንደ ፈለጋችሁ መነገድ ትችላላችሁ።’ ”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ታና​ሹ​ንም ወን​ድ​ማ​ች​ሁን አም​ጡ​ልኝ፤ ሰላ​ማ​ው​ያን እንጂ ሰላ​ዮች አለ​መ​ሆ​ና​ች​ሁ​ንም በዚህ ዐው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በሀ​ገ​ራ​ችን ትነ​ግ​ዳ​ላ​ችሁ።’ ”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ታናሹንም ወንድማችሁን አምጡልኝ እውነተኞች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁንም በዚህ አውቀዋለሁ ወንድማችሁንም እሰጣችኍለሁ እናንተም በምድሩ ትነግዳላችሁ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 42:34
7 Cross References  

ከእኛም ጋር ተቀመጡ፥ ምድሪቱም እንደፈለጋችሁ ሁኑባት፥ ኑሩባት፥ ነግዱባትም፥ ሀብትም አፍሩባት።”


“እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው፥ በምድራችን ይቀመጡ፥ ይነግዱባትም፥ እነሆም ምድሪቱ ሰፊ ናት፥ ሴቶች ልጆቻቸውን እንውሰድ፥ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻችንን እንስጥ።


ቀንበጡንም ቀነፈ፥ ወደ ከነዓንም ምድር አመጣው፥ በነጋዴዎችም ከተማ ተከለው።


ይህም ሁሉ ነጋዴዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፥ ከንግድ ከሚገኘው ትርፍ፥ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ጋር ተጨማሪ ነበር።


ታናሽ ወንድማችሁን ግን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፤ በዚህም የተናገራችሁት ቃል እውነተኛነት ይረጋገጣል፤ እናንተም ከመሞት ትተርፋላችሁ።” እነርሱም ይህንኑ ለመፈጸም ተስማሙ።


አቢሜሌክም፦ “እነሆ፥ ምድሬ በፊትህ ናት፥ በወደድኸው ተቀመጥ አለ።


ታናሽ ወንድማችሁ እዚህ እስካልመጣ ድረስ ከዚህ ንቅንቅ እንደማትሉ በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ ማንነታችሁ የሚረጋገጠውም በዚህ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements