Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 41:52 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 እንደዚሁም፥ “መከራ በተቀበልኩበት ምድር እግዚአብሔር ፍሬያማ አደረገኝ” ሲል ሁለተኛ ልጁን ኤፍሬም አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 እንደዚሁም፣ “መከራ በተቀበልሁበት ምድር እግዚአብሔር ፍሬያማ አደረገኝ” ሲል ሁለተኛ ልጁን ኤፍሬም አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 እንዲሁም “መከራ በተቀበልኩበት ምድር እግዚአብሔር ልጆች ሰጠኝ” በማለት ሁለተኛውን ልጅ ኤፍሬም ብሎ ጠራው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 የሁ​ለ​ተ​ኛ​ው​ንም ስም ኤፍ​ሬም ብሎ ጠራው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ከ​ራዬ ሀገር አብ​ዝ​ቶ​ኛ​ልና።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 የሁለተኛውንም ስም ኤፍሬም ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል፦ እግዚአብሔር በመከራዬ አገር አፈራኝ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 41:52
21 Cross References  

ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ፥ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ።


የኤፍሬምንም ልጆችና የልጅ ልጆች እስከሚያይ ድረስ ቈየ፤ ከምናሴ የተወለደውንም የማኪርንም ልጆች እንደ ልጆቹ አድርጎ ተቀበላቸው።


እጅግም አበዛሃለሁ፥ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ።


ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን ይባርክህ፥ ያፍራህ፥ ያብዛህ፥


በፋጋ የወይን ጠጅ ለምትጠጡ፥ እጅግ ባማረ ቅባትም ለምትቀቡ፥ ስለ ዮሴፍ መከራ ግን ለማታዝኑ ለእናንተ ወዮላችሁ!


ከመከራውም ሁሉ አወጣው፤ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖንም ፊት ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፤ በግብጽና በቤቱ ሁሉ ላይም ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።


ዮሴፍም፥ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ፥ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ አለው።


በግብጽ ምድር የነበረው ሰባቱ የጥጋብ ዘመን ዐለፈና


ጥቂት ጊዜ ካለፈ በኋላ “አባትህ ታሞአል” ተብሎ ለዮሴፍ ተነገረው፤ ስለዚህ ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ያዕቆብን ለማየት ሄደ።


እስራኤልም ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረው፥ እርሱም ታናሽ ነበረ፥ ግራውንም በምናሴ ራስ ላይ አኖረ፥ እጆቹንም አስተላለፈ፥ ምናሴ በኩር ነበርና።


ስለዚህ ሐና ፀነሰች፤ የእርግዝናዋ ወራት በተፈጸመ ጊዜም ወንድ ልጅ ወለደች፤ “ከጌታ ለምኜዋለሁ” ስትል ስሙን “ሳሙኤል” ብላ ጠራችው።


አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብጽ ምድር የተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችህ ለእኔ ይሁኑ፥ ኤፍሬምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ናቸው።


በየወገናቸው የዮሴፍ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ምናሴና ኤፍሬም።


የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንሰሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን ማሰማርያ በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም።


የዮሴፍም ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን ወረሱ።


ለምናሴ ነገድ ዕጣው ይህ ነው፤ የዮሴፍ በኩር እርሱ ነውና። የምናሴም በኩር የገለዓድ አባት ማኪር ብርቱ ተዋጊ ስለ ነበረ ገለዓድንና ባሳንን ወረሰ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements